‹‹ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ክልሎችን እየለመንን መቀጠል አንችልም›› ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሰላም ሚኒስትር

በዜጎች ደም ሀብት የሚያጋብሱ አሉ ብለዋል

ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨትና በማፈናቀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ክልሎች እየተባበሩ እንዳልሆነ፣ ከዚህ በኋላ ግን ክልሎችእንዲተባበሩ በመለመን መቀጠል እንደማይቻል የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ማክሰኞ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ነው።

ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨትና በማፈናቀል ወንጀል የተጠረጠሩ ከ800 በላይ ግለሰቦች መኖራቸውን፣ እስካሁን ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በሕግ ቁጥጥር ሥርየዋሉት 50 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት የክልል አመራሮችና የፀጥታ ተቋማት ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነአስረድተዋል።

ከፌዴራል መንግሥት ሕግ አስከባሪ አካላት በተሻለ ተጠርጣሪዎቹ የት እንደሚገኙ መረጃ ያላቸው የክልል የፀጥታ አካል እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ የክልልየፀጥታ ተቋማት ግን ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና የፖለቲካ ቁርጠኝነትም ባለመኖሩ፣ በተለይም በፖለቲካ አመራርነትና በፀጥታ አስከባሪነት የሥራኃላፊነቶች ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎችን መያዝ እንዳልተቻለ አስታውቀዋል።

‹‹ትብብር መጠየቃችን ተገቢ አካሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ክልሎችን በመለመን መቀጠል አይቻልም፤›› ብለዋል። ስለሆነም ለዚህ ተብሎ የተደራጀ ልዩኃይል የሚፈልጉ አካባቢዎች ገብቶ መሥራት መጀመሩን ገልጸዋል።

ይህ ኃይል ተደራጅቶ ሥምሪት ከመውሰዱ በፊት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ባለባቸው እንደ ቤንሻንጉል ጉምዝና ሶማሌ ክልሎች፣ እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማአስተዳደር ባሉ አካባቢዎች የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች በአመዛኙ መያዛቸውን አስረድተዋል።

ለምሳሌ በሶማሌ ክልል ሕዝቦችን በማጋጨትና በማፈናቀል የተጠረጠሩ በክልሉ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ከሞላ ጎደል መያዛቸውን፣ ከአገር የወጡተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ የሰላም ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከኢንተርፖል ጋር የተጀመረው ትብብር በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠረጠሩትን ብቻ ለመያዝ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በተመሳሳይ ወንጀሎችየሚፈለጉና ከአገር የወጡትን በሙሉ የሚመለከት እንደሆነ አስረድተዋል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚፈለጉ 180 ተጠርጣሪዎች መካከል 171 የሚሆኑት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ፣ ከእነዚህም ውስጥ 23 በክልሉ የፖለቲካናየፀጥታ ዘርፎችን በአመራርነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 50 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ ተጠርጣሪ በከተማው የአንድ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊመሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባና በቡራዩ ከተሞች ተፈጥሮ በነበረው ግጭትና መፈናቀል 108 ተጠርጣሪዎች የሚፈለጉ መሆኑን፣ ከእነዚህ ውስጥ 85 በቁጥጥር ሥር ሲውሉ23 አለመያዛቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስት የወረዳ የፖለቲካ አመራሮችና አንድ የፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

በኦሮሚያ በጉጂ ሕዝቦችን በማጋጨትና በማፈናቀል 312 ግለሰቦች የተጠረጠሩ ቢሆንም፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተቻለው ዘጠኝተጠርጣሪዎችን ብቻ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በደቡብ ክልል በሸካ ዞን ተፈጥሮ በነበረው ግጭትና ማፈናቀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች 97 እንደሆኑ፣ ነገር ግን እስካሁን በሕግቁጥጥር ሥር የዋሉት አሥር ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዳይውሉ ከለላ እንደሚደረግላቸው፣ ከተፈናቀሉ ነዋሪዎች መካከል ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ፍላጎት በሚያሳዩት ላይድብደባ እንሚፈጸም የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ ‹‹ይህ የሚደረገው ጫካው ከተመነጠረ አመራሮቹና ተጠርጣሪዎቹ ዕርቃናቸውን ስለሚቀሩ ነው፤›› ብለዋል።

አንዳንድ ክልሎች ደግሞ ለተጠርጣሪዎቹ ከለላ ባይሰጡም፣ ተጠርጣሪዎቹ የነፃነት አርበኞች እንደሆኑ አድርገው ለመሳል የሚዲያ ዘመቻ እንደሚከፍቱተናግረዋል።

አንዱ ወንጀል ከሌላ ወንጀል ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፣ የአገሪቱን የፀጥታ ችግር ውስብስብ አድርጎታል ብለዋል።

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የጦር መሣሪያ፣ የውጭ ምንዛሪ ዝውውርና ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት የማፈናቀል ተግባራት ዝምድና እንዳላቸው መረጋገጡንገልጸዋል።

ለአብነትም በአንድ ስሙን ባልጠቀሱት አካባቢ ያለ አንድ አመራር፣ በኮንትሮባንድ የተያዘ ቁሳቁስ በመሸጥ የጦር መሣሪያ ግዥ እንደፈጸመ ጠቁመዋል።

ሕዝቦችን የማጋጨትና የማፈናቀል፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የውጭ ምንዛሪ ዝውውርና ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርና ንግድ ለማከናወን ምቹ ሁኔታንእንደሚፈጥር፣ ለተፈናቃዮች ተብሎ የሚገኘው የውጭ ዕርዳታ እንዳይቋረጥ በማድረግ ከዕርዳታ አቅርቦት የድርሻቸው ገቢ እንዲቀጥል ማድረግ ደግሞ፣ሌላው የወንጀሎች ባህርይ መሆኑን አስረድተዋል።

ሁኔታውን አጠቃለው ሲገልጹትም፣ ‹‹በዜጎች ደም ሀብት የሚያጋበሱ አሉ፣ የእነሱ ሴራ ነው፤›› ብለውታል።

የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ጥረት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን፣ ባለፋት ዘጠኝ ወራትም 875 ሺሕ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸውእንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል።

ምንጭ፡ ሪፖርተር

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe