ቱርክ ከዩናይትድ ኪንግደም በ11 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተዋጊ ጄቶችን ለመግዛት ተስማማች

ከኔቶ አገራት ውስጥ ድሮኖችን በመሸጥ ሁለተኛዋ ሀገር ቱርክ አሁን 20 ተዋጊ ጄቶችን ለመግዛት ያስታወቀችው።
ቱርክ ከአሜሪካ በመቀጠል TB2 የተባሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለተቀረው ዓለም በማቅረብ ከኔቶ አባላት ሁለተኛዋ ሀገር ናት። ቱርክ በግሎባል የድሮን ቴክኖሎጂ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የምትይዝ ሀገርም ጭምር ነች።
ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን 20 ኢሮ ተዋጊ ጄቶችን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።
አንካራ ይህን በማድረግ የአየር መከላከያ ስርዓቷን ለማጠናከር ጥረት ላይ ስለመሆኗ አልጀዚራ ዘግቧል። አንካራ ከእንግሊዝ ከምትገዛቸው ታይፎን ተዋጊ ጄቶች ውጪ በራሷ የሚመረቱ የአምስተኛው ትውልድ ተብለው የሚጠሩ ካን ተዋጊ አውሮፕላኖች ያሏት እንደሆነች ይታወቃል።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ትላንት በአንካራ የነበሩ ሲሆን ከፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ጋርም ስምምነቱን ፈርመዋል። የዩናይትድ ኪንግደሙ የመከላከያ ሚኒስቴር የጀነሬሽኑ የተዋጊ ጄት ስምምነት ብሎታል። ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን ደግሞ ስምምነቱ በሁለት ወዳጅ ሀገራት መካከል የተደረሰ እንደሆነ ገልጸው፤የአዲስ ስትራቴጂክ ምልክት ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ሰምምነቱ ሁለቱም ሀገራት አባል የሆኑበት ኔቶ አሸናፊነት ነው ብለዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚስትሩ ገለጻ እነዚህ የታዘዙት የታይፎን ተዋጊ ጄቶች በ20230 በአንካራ ይደርሳሉ።
የቱርክ ባለስልጣናት አንካራ 120 ተዋጊ ጄቶችን በመግዛት አቅሟን ማጠናከር ትፈልጋለች።
ከዚህ ውጭ ቱርክ በመጪዎቹ ዓመታት እነዚህ የታይፎን ጄቶች ከእንግሊዝ እስኪገቡ ድረስ ከኦማን እና ከኳታር በመጠኑ ያገለገሉ 12 የታይፎን ጄቶችን ገዝቶ የማስገባት ፍላጎቱ እንዳላት ተሰምቷል።
ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን በዚህ ጉዳይና በሌሎችም ለመነጋገር በኦማን እና በኳታር ጉብኝት ማድረጋቸው አይዘነጋም።
ባለፈው ዓመት ቱርክ ከዩናይትድ ስቴትስ 40F-16 ጄቶችን በ7ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ስምምት ያደረገች ቢሆንም መዘግየቱን ዘገባው አስታውሷል።
በእስራኤል የሚደርሱ የአየር ጥቃቶች ቱርክን ጨምሮ ሊባኖስን ኳታርን እንዲሁም ሌሎቹን ጨምሮ መሳሪያዎችን እንዲታጠቁ እያደረጋቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በሌላ ዜና ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ክፉኛ ተመታለች ተባለ። የሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በመሬት መንቀጥቀጥ መናጡን ዘገባዎች አመላክተዋል።
አደጋውን ተከትሎ ይህ ዘገባ እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 22 ሰዎች ተጎድተዋል፤ህንጻዎች ተደርምሰዋል።
ሰኞ ጠዋት ምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል 6.1 በተለካ ማግኒቲዩድ ተመቷል። እንደ ዘገባዎቹ መረጃ እስካሁን ቢያንስ ሦስት ህንጻዎች ወድመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe