” ቲክቶክ ” ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ

የኬንያ ፓርላማ ” #ቲክቶክ ” የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

” ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ ‘ቲክቶክ’ ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው ” የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ ” ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን የሚያበረታቱ ” እና ” የብልግና ” እና ” መረን የለቀቀ ጾታዊ ይዘት ” ያላቸው የ ” ቲክቶክ ” ተንቀሳቃሽ ምስሎች ” በኬንያ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል” በማለት አቤቱታውን ደግፈው መናገራቸው ተዘግቧል።

የኬንያ ፓርላማ በአቤቱታው ላይ ውሳኔ ባይሰጥም ፤ የመጀመሪያ ውይይት ግን እንዳደረገበት ተጠቁሟል።

ኬንያ በአፍሪካ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚ ናት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe