አትሌት ትዕግስት ግርማ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው የኢትዮጽያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1ሺ500 ሜትር ክለቧን መቻልን በመወከል 2ኛ በመውጣት ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡
አትሌት ትዕግስት ከዚህ ወድድር ከተመለሰች በኋላ ለጃፓኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ለማሟላት ወደ ሌላ ውድድር ልታቀና በተሰናዳችበት እለት ነው በኤርፖርት በቁጥጥስር መዋሏ የተሰማው፡፡
ትዕግስት ለጃፓን ቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ለማምጣት ወደ ኳታር ዶሃ ዳይመንድ ሊግ በማቅናት ላይ እያለች ነው በቦሌ ኤርፖርት በክለቧ በተጻፈ ደብዳቤ መሠረት በቁጥጥር ስር የዋለችው ተብሏል፡፡
የእስሩ ምክኒያትም አትሌት ትዕግስት ከዚህ በፊት የክለቧን ፈቃድ ሳታገኝ ወደ አውሮፓ ለውድድር በመሄዷ ሳይሆን እንዳልቀረ ኢትዮ ራነርስ የተሰኘ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ነገር ግን አትሌት ትዕግስት ያለ ፈቃድ ወደ አውሮፓ እንዳልሄደች መግለጻም በዘገባው ተካቷል፡፡

