ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ሆኑ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ፤ ” ከየካቲት 2012 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው የኤክሳስ ታክስ አዋጅ ያስገኘውን ጠቀሜታ እንዲሁም የታዩትን ክፍተቶች በመገምገም በአንዳንድ ምርቶች ላይ የተጣለውን የማስከፈያ ምጣኔ ማስተካከል ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ የአዋጁ ማሻሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል ” ብሏል።

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላም ግብዓቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

#ማስታወሻ ፦

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ አይዘነጋም።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ የነበረው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

– በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤
– ከ3000 ሲሲ ባላይ ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤
– ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤
– ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤
– ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

ከዚህ በተጨማሪ ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ያደርጋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe