የኢራን ባሕር ኃይል ከትናንት ጀምሮ ከ30 በላይ መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን እንዲያልፉ መፍቅዱን አስታወቀ።የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደዘገበዉ ከትናንት ሮብ ጀምሮ እስከ ዛሬ ቀጥር ድረስ ከ30 የሚበልጡ መርከቦች የተዘጋዉን የባሕር ወሽመጥ አልፈዋል።
የኢራን ቴሌቪዥንን ጠቅሶ የዘገበዉ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የመርከቦቹን ትክክለኛ ቁጥርና የባለቤቶቻቸዉን ማንነት አልጠቀሰም።የኢራን ዜና አገልግሎት ታስሚን በበኩሉ እንደዘገበዉ ከትናንት ማታ ጀምሮ በርካታ የቻይና መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸዋል።በዜና አገልግሎቱ ዘገባ መሠረት የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦቹ እንዲያልፉ የፈቀደዉ ቻይና ለኢራን ባቀረበችዉ ጥያቄና በቴሕራን ፈቃድ መሠረት ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ካለፈዉ የካቲት ማብቂያ ወዲሕ የኢራን ጦር በርካታ ሸቀጥ የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥን ዘግቷል።የባሕር ወሽመጡ በመዘጋቱ ከ20 ሺሕ በላይ መርከቦች መተላለፊያ አጥዉ ባሕር ላይ እየቀዘፉ ነዉ።

