ቴክኖ ሞባይል አዳዲስ የስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልኮች በኢትዮጵያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ግንቦት 5፣ 2015 – በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች ኣምራች የሆነው ቴክኖ
ሞባይል በዛሬው እለት አዳዲሶቹን የስፓርክ 10 ሲሪየስ ሞዴሎች በኢትዮጵያ የማስተዋወቅ ልዩ ዝግጅት በማድረግ ለተጠቃሚዎች
ይፋ ኣደረገ።
ኢትዮጵያ ጨምሮ ከ70 በላይ አለም አቀፍ ገበያዎች ላይ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያፈራው ቴክኖ ሞባይል በዛሬው እለት
በተከፈተው አና ለሁለት ቀናት የሚቆየው ዝግጅት ይበልጥ የዘመኑ ገፅታዎችን በመያዝ አንዲሁም የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ከግምት
በማስገባት የተመረቱትን የስፓርክ 10 ፣ ስፓርክ 10ሲ እና ስፓርክ 10ፕሮ ሞዲሎች ለገበያ አቅርቧል። ቴክኖ ስፓርክ ሲሪየስ አሁን
ደግሞ ይበልጥ የዘመኑ መገልገያዎችን በመያዝ አንዲሁም የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ከግምት በማስገባት ዘመናዊ የፊት ለፊት ካሜራን፣
ወቅታዊ ዲዛይን እና ፈጣን ፕሮሰሰር በመጠቀም ለተገልጋዮች ቀርቧል።

TECNO Unveils the Spark 10 Series Smartphones in Ethiopia

ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ ሆኖ የተሰራው የስፓርክ 10 ሲሪየስ ሞዴል በተለይ በባለ 32 ሜጋ ፒክስል የፊትለፊት ካሜራ፣ ዘመኑ
ያፈራው ሚዲያቴክ G88 ጌም ፕሮሰሰር ፣ ብሎም ረጅም የአገልግሎት ጊዜ እንዲኖረው ታስቦ የተገጠመለት በባለ 5000 ሚሊ
አምፒር ባትሪ በሁሉም ረገድ ከፍተኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተመረተ ስልክ አድርጎታል።
ስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ ሞዲሎች በተሻሻለ ጥራት በተፈበረኩት የፊትና የሗላ ካሜራዎቹ ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ የተሰሩ
ሲሆኑ በተለይም ስፓርክ 10 ፕሮ በባለ 50 ሜጋ ፒክስል ዋና ካሜራ ሲይዝ የፊት ለፊቱ ጥራት ያለው ፎቶ ያለ እንከን ቁልጭ አርጎ
ማንሳት የሚችል ብሎም በብርሀን ማነስ የማይገደብ ልዩ የሆነ በባለ 32 ሜጋ ፒክስል ሰልፊ ካሜራ ከፍላሽ መብራት ጋር የያዘ
ነው። በተጨማሪም የትኛውንም ዓይነት ትላልቅ ጌሞችን ያለ ምንም እንከን አንዲጫወቱ ያስችል ዘንድ በጌም ቱርቦ አልጎሪዝም
የተደገፈ በባለ 8 ኮር G88 ጌሚንግ ቺፕ ከ6.8 ኢንች ስክሪን ጋር ለገበያ ቀርቧል።
ቴክኖ ሞባይል ለገበያ ያቀረበው ማራኪ ዲዛይን ጥራት ያለው ባለ 6.8 ኢንች ስክሪን ልዮ ስታሪ ግላስ የተባለ ብርጭቆ ፓናል
የተላበሰ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ጭረት እንዲቋቋም እና ለእይታ ማራኪ ያደርገዋል። የዚህ ምርት ትኩረት በውጫዊ ውበት ላይ ብቻ
የተወሰነ ሳይሆን ይልቁንም ለወጣቱ ትውልድ በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲኖራቸው፣ ለራሳቸው ገደብ እንዳይሰጡ፣
ስብዕናቸውን እና አመለካከታቸውን በመግለፅ ችሎታቸውን ገፍተው በመሄድ እውነተኛ ማንነታቸውን በልበ ሙሉነት እንዲያሳዮ
የሚያበረታታ መልዕክት አካቶ ይዟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe