ቴክኖ  ሞባይል የ ኤ አይ  አጋዥ መተግበሪያንና አዳዲስ በኤ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋወቀ

ቴክኖ በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀውን የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን  ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል አስተዋውቋል፡፡

አዲሱ የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ ቴክኖሊጂ የዕለት ተዕለት ኑሮን በእጅጉ ከማቅለሉም በላይ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመከወን የሚያስችል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴከኖሎጂን ተካቶለታል፡፡

መርሐግብሩን የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር ሚስተር  አሊክ በመከፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ቴክኖ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሚሽን ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን እየተጫወተም እንደሚገኝ እና በዚህም ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው ተናግረዋል፤ አክለውም ቴከኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በታዋቂው የቴኖሎጂ ኤክስፐርት አቶ ሰለሞን ካሳ ስለ አዲሶቹ የፋንተም V2 የታጣፊ ስልኮች ከቴክኖ ኤ አይ ጋር አጣምረው ስለመጡት ቴከኖሎጂ በምስል የታግዘ ሰፊ ማብራሪያ ለታዳሚው የተሰጠ ሲሆን የዝግጅቱ ታዳሚዎች የቴከኖ ኤ አይ እና አዲሶቹ የፋንተም V2 ታጣፊ ስልኮችን በቅርበት የመመልከት ዕድልም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪ ከኤ አይ ቴከኖሎጂ ጋር የተገናኙ እንደ VR ያሉ የኤይ አይ ቴከኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጌሞች ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የስልኮቹን የካሜራ ብቃት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ቀርቧል፡፡

ቴክኖ ከአለም የቴክኖሎጂ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ እና ከፍ ያለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ወደ ተጠቃሚ ማድረሱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በኤይ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለተጠቃሚዎች አጅግ ቀላል እና ዘመናዊ የምርት ውጤትን ለመስጠት እየተጋ ይገኛል፡፡

በማስተዋወቂያ መርሐግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የቴከኖ ኢትዮጵያ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe