ቴክኖ በአይነቱ አዲስ የሆነ እና ሶስት ጊዜ የሚታጠፍ PHANTOM ULTIMATE 2 የተሰኘ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሀሳብን ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሃሳብ በአለም ገበያ ላይ ከሚገኙ ታጣፊ ስልኮች ቀጭን ዲዛይን ያለው ሲሆን ስልኩ ሶስት ጊዜ የመታጠፍ ብቃት ሲኖረው 11 ሚሊ ሜትር ውፍረት ብቻ እንዲኖረው ሆኖ ዲዛይን ተደርጓል፡፡
PHANTOM ULTIMATE 2 ሲታጠፍ 6 ነጥብ 48 ኢንች ሙሉ በሙሉ ሲዘረጋ ደግሞ 10 ኢንች የስክሪን ስፋት ይኖረዋል ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ስራዎችን በአንድ ጊዜ ከፋፍሎ ለመስራት የሚያስችለው ይህ ስልክ በኤ አይ ቴክኖሊጂ በመጠቀም ሁለት ስራዎችን እንደ አንድ ለመከወን እና የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመተርጎም የሚያስችል ብቃትም አለው፡፡
ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ግብዕቶች የተሰራው PHANTOM ULTIMATE 2 በመታጠፍ ብዛት እንዳይበላሽ ተደርጎ ዲዛይን ከመደረጉም ባሻገር ቀድሞ ከነበሩት የታጣፊ ስልክ ዲዛይኖች ከፍ ያለ የካሜራ፣ የሶፍትዌር እና የባትሪ ጥራት እንዲኖረው ተደርጎ ተሰርቷል፡፡
ይህ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሃሳብ በቅርብ ለአለም ገበያ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

