ዝነኛው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከእስራኤል የሙዚቃ ዝግጅቱ መልስ በሌላ የሙዚቃ ዝግጅት መምጣቱን ገለጸ፡፡ ቴዲ አፍሮ ከሳምታት ገደማ በፊት እስራኤል የነጻነት ቀን በዓሏን ስታከብር በእስራኤል ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጽያዊያንና ለቤተ-እስራኤላዊያን የሙዚቃ ስራውን አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አሁን ከዚያ የሙዚቃ ዝግጅት መልስ ነው ቴዲ የፊታችን እሁድ በአሜረካ ዲኤም ቪ አካባቢ የሙዚቃ ስራውን እንደሚያቀርብ ይፋ ያደረገው፡፡
በእስራኤል የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት በስከት የተጠናቀቀ እንደነበርም ተሰምቷል፡፡ ብዙ አድናቂዎችን ይዞ ዓመታትን መዝለቅ የቻለው ቴዲ በርካታ አድናቂዎቹ ወደ ሚገኙበት አሜሪካ ከአቦጊዳ ባንድ ጋር ተጉዟል እሁድ እለትም የሙዚቃ ዝግጅቱ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡//

