ትራምፕ እና ኔትንያሁ በኢራኑ ጦርነት ዙሪያ ወደ አለመግባባት ገብተዋል ተባለ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ በኢራኑ ጦርነት ዙሪያ ወደ አለመግባባት ገብተዋል ተባለ፡፡

የካቲት 21 ላይ በጋራ ጦርነት በኢራን ላይ ባወጁት ትራምፕ እና ቤኒያሚን ኔትንያሁ መካከል ያላግባባ አንዳች ነገር ስለመፈጠሩ መገናኛ ብዙሃን በዘገባዎቻቸው አስታውቋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ በኢራን ላይ የሚደረገው ጦርነት ተጠናክሮ ይቀጥል የሚል ሃሳብ ሲያነሱ፤ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ ለዲፕሎማሲ ፋታ እንስጥ የሚል አቋም እንዳንጸባረቁ ተነግሯል፡፡ ሁለቱ መሪዎች በስልክ ስለ ኢራኑ ጦርነት የወደፊት አቅጣጫ በስልክ በተወያዩበት ወቅት ነው እንዲህ አይነቱ ልዩነት የተስተዋለው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ለጊዜውም ቢሆን እንዲገቱ የፈለጉት የገልፍ ሀገራት አሁን ነገሮች በሰላም ስምምነት የማለቅ እድላቸው ሰፊ ነውና አዲስ ጥቃቶች ይቁሙ በሚል ባቀረቡላቸው ጥያቄ መሠረት እንደሆነ ማክሰኞ እለት በይፋ መናገራቸው ይታወቃል፡፡

ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔው ነው ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ ምቾት ያልሰጠ ጉዳይ የሆነው፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት ዕረቡ ለሪፖርተር እንዳሉት የኢራን ጉዳይ አሁን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው፤ቀጥሎ ምን እንደሚፈጠር አብረን እናያለን ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል  ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ በኢራን ጉዳይ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ ለኢራን እየተሰጠ ያለው ፋታ የኢራንን አቅም እንዲጠናከር ከማድረግ የዘለለ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ያምናሉ፡፡ እናም በዚህ የተነሳ ነው በትራምፕ እና በኔትንያሁ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል የተባለው፡፡

እንዲህ አይነቱ የሃሳብ ልዩነት በዋሽንግተን እና በቴላቪቭ ሲፈጠር የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ የአሜሪካ ባለስልጣናት ቀደም ባሉት ጊዚያት እንደተናገሩት ወዳጆቹ አሜሪካ እና እስራኤል ሁልጊዜ ኢራንን በተመለከተ አንድ አይነት ዓላማ ይኖራቸዋል ማለት አይደለም ብለው ነበር፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ትላንት እንዳሉት ቴህራን እና ዋሽንግተን በፓኪስታን አማካኝነት መልዕክቶችን መለዋወጥ መቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በሁለቱ ተደራዳሪ ሃይሎች መካከል ያለው ፍላጎት ግን የተራራቀ እንደሆነ እየተነሳ ነው፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ እና እስራኤል መልሰው ጥቃት የሚፈጽሙ ከሆነ እናተ ከምታስቡት በላይ ከባድ ምት አደርሳለሁ በማለት እያስጠነቀቀ ነው፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe