ትራምፕ ከሁሉም ሶስተኛ ዓለም ሀገራት የሚደረገውን ፍልሰት በቋሚነት አስቆማለሁ አሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደራቸው ከሁሉም ሶስተኛ ዓለም ሀገራት የሚደረገውን ፍልሰት በቋሚነት ለማስቆም እና ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች የሚያገኟቸውን የፌዴራል ጥቅማጥቅሞች እና ድጎማዎች ለማቆም እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የአገር ውስጥ ሰላምን አደጋ ላይ የሚጥሉ ስደተኞችን ዜግነታቸውን ለመንጠቅ (denaturalize) እና ለደህንነት አስጊ የሆኑ ወይም ከምዕራባውያን ስልጣኔ ጋር የማይጣጣሙ ተብለው የተፈረጁትን ከሀገር ለማስወጣት (deport) ማቀዱን አክለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐሙስ ዕለት እንዳሉት የአሜሪካ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ እንዲያገግም ለማድረግ አስተዳደራቸው ከሁሉም ሶስተኛ ዓለም ሀገራት የሚደረገውን ፍልሰት በቋሚነት ለማቆም ይሰራል።
ትራምፕ በ ትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ በተጨማሪም ዜግነት ለሌላቸው ግለሰቦች የሚሰጡትን ሁሉንም የፌዴራል ጥቅማጥቅሞች እና ድጎማዎች እንደሚያስቆሙ ተናግረው የአገር ውስጥ ሰላምን የሚያናጉ ስደተኞችን ዜግነት እንደሚያስነጥቅ እንዲሁም ሕዝባዊ ሸክም ለደህንነት አደጋ ወይም ከምዕራባውያን ስልጣኔ ጋር የማይጣጣም ማንኛውንም የውጭ ዜጋ ከሀገር እንደሚያስወጣ አክለዋል።
የትራምፕ አስተያየት የመጣው ሐሙስ ዕለት በዋይት ሀውስ አቅራቢያ በተፈጸመ ጥቃት በጥይት ተመትቶ የሞተውን የብሔራዊ ዘብ አባል ተከትሎ ሲሆን መርማሪዎች ጥቃቱን የፈፀመው የአፍጋኒስታን ዜጋ ነው ብለዋል።

