“ያልፈታሁት ብቸኛው ግጭት የሩሲያ-ዩክሬን ነው፡፡ ግን ይፈታል፡፡ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ባለን ግንኙነት የተነሳ ቀላል እንደሚሆን አስቤ ነበር። ትንሽ የተለየ ሆኖ ተገኝቷል። ግን ይፈታል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ትራምፕ በዩክሬን ዘላቂ ሰላም እንደሚፈልጉ እና ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እንደማይሹ ሩሲያ ተስፋ ታደርጋለች ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረዋል፡፡
🔊 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪየቭ ትራምፕ በዩክሬን ሰላም ስምምነት ላይ የሚያደርጉት ጥረት ከንቱ እንዳልሆነ ባለፈው ሳምንት ተናግረዋል።

