ትራምፕ 30,000 ሰነድ አልባ ስደተኞችን በጓንታናሞ ቤይ ለማሰር ማቀዳቸውን ገለፁ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን በጓንታናሞ ቤይ ለማሰር ማቀዳቸውን ገልፀዋል።
ትራምፕ ስለ ዕቅዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገሩት በስርቆት ወንጀሎች የተከሰሱ እና ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች እንዲታሰሩ የሚደነግገውን የላርኪን ሪሌይ አክትን ሲፈርሙ ነው።
በጓንታናሞ ቤይ ውስጥ እስከ 30,000 የሚደርሱ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን እንደሚያስሩ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ በሕገ-ወጥ ስደት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
ይህ ዕቅድ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው በሕገ-ወጥ ስደት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የገቡትን ቃል እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ትራምፕ ስለ ዕቅዳቸው ሲናገሩ “ለአሜሪካ ህዝብ ስጋት የሆኑ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ለማቆየት በጓንታናሞ 30,000 አልጋዎች አሉን፤ ይህም ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን የመያዝ አቅማችንን በእጥፍ ያሳድጋል” ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe