ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለገና በዓል ያለቪዛ ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ተፈቀደ

መንግስት ለገና በዓል አንድ መሚሊየን ኢትዮጵያውያን፤ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበዓል ወደ ሀገር ቤት ለሚመጡ መንገደኞች የ30 ከመቶ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በበኩሉ   እንግዶቹን ለመቀበል ከጉዞ ሰነድ ጋር የተያያዘ ችግሮችን  አስወግዳለሁ ብሏል፡፡

የአገልግሎቱ  ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል እንደተናገሩት ፦

  • የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የታደሰ ሆነ የአገልግሎት ግዜው ያለፈበት ቢሆንም ወደ ሀገር ቤት መግባት ይችላሉ፣
  • በልዩ ሁኔታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ትችላላችሁ ነው ያሉት፤
  • ያም ሆኖ ይላ ዋና ዳይሬክተሩ የታደሰም ሆነ ግዜው ያለፈበትን መታወቂያ ኤርፖርት በኢሚግሬሽን ካውንተር ላይ ስለምትጠየቁ በእጅዎ መያዞትን አይዘንጉ ብለዋል።
  • የሌላ አገር ፓስፖርት የያዛችሁና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የምትፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ከፈለጋችሁ አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት http://xn--www-86o.digitalinvea.com/ ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት ትችላለችሁ ተብሏል፤

– ተቋሙ በተለየ መልኩ ከ15 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ እናንተ በሞላችሁት አድራሻ ድረስ በመላክ አገልግሎት ይሰጣችኋል ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

  • ከዚህ በፊት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ለሌላቸው ወገኖችም አገልግሎቱ ሌላ መልካም ዜና አለው፤ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመያ ካርድ ወይም ቢጫ ካርድ የሌላችሁ ደንበኞች የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት በ www.evisa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ በማመልከት በፍጥነት አግልግሎቱን ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

በሂደቱ ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግሮች support@evisa.gov.et በሚል የኢሜል አድራሻችን ላይ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ።

  • ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ለምትገቡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመዳረሻ ቪዛ/on arrival visa/ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ኤርፖርት ላይ የሚቆዩትን ግዜና ድካምዎን ለመቀነስ በኦንላይን ላይ ቀደም ብለው እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ ብሏል አግልግሎቱ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe