ቻይናዊያን አግብተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ኢትዮጽያዊያን ሴቶች ችግር ውስጥ እየወደቁ ነው ተባለ

በቻይናዊያን እና በኢትዮጽያዊያን ደላሎች አመቻችነት ይፈጠራል በተባለው ጋብቻ ወደ ቻይና የሚሄዱ ሴት ኢትዮጽያዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደመጣ በቻይና የኢትዮጽያ ኤምባሲ ገልጻል፡፡

በደላሎች አማካኝነት ኢትዮጽያዊያን ሚስት የሚላክላቸው ቻይናዊያኑ ቋሚ ገቢም ሆነ ኑሯቸውን ለመምራት የሚያስችል ገቢ የሌላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

በዚህ መሠረትም ኢትዮጽያዊያኑን ወደ ገጠራማ አካባቢ በመውሰድ ከቤተሰቦቻው ጋር እንዲኖሩ እንደሚያደርጓቸው ኤምባሲው ባደረገው ጥናት መረዳቱን ገልጻል፡፡

ኢትዮጽያዊኑ ይህንን ጋብቻ ፈጽመው ወደ ቻይና የሚሄዱት የተሻለ ህይወት ጠብቀው ነው ነገር ግን ቻይና እየገጠማቸው ያለው ይሄ ነው ብሏል፡፡ በዚህ መንገድ ወደ አገሪቱ የገቡ ኢትዮጽያዊያን ስራ እንዲሰሩ የቻይና ህግ አይፈቅድላቸውም፡፡

ቻናይዊያን ወንዶች ኢትዮጽያዊያን ሴቶችን ለጋብቻ የሚመርጡት በባህላቸው የሚጠየቀውን ከፍተኛ የሆነ የጥሎሽ ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው እንደሆነም ኤምባሲው ገልጻል፡፡

በዚህ መንገድ ወደ ቻይና ከሄዱት ኢትዮጽያዊያን ውስጥ ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ኤምባሲው እንዲያወጣቸው ቢያንስ በሳምንት አንድ ሴት ይህን ጥያቄ ታቀርባለች ብሏል፡፡

ኤምባሲው በዚህ ወቅት በህይወት እንዲመለሱ ለማድረግ እያደረገ ባለው ጥረት አንድ ኢትዮጽያዊት በሳምንት ከዚህ ሁኔታ እንድትወጣ በማድረግ ወደ ኢትዮጽያ እየመለሰ እንደሆነም አስታውቋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe