ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በራሷ ባለሙያዎች የተሰራ የመንገደኞች አውሮፕላን ስራ ላይ አዋለች

ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ C919 የተሰኘ በራሷ ባለሙያዎች የተሰራ የትራንስፖርት አውሮፕላን ስራ ላይ ማዋሏን አስታወቀች፡፡
አውሮፕላኑ ከሻንግሀይ ወደ ቻይና መዲና ቤጂንግ የተሳካ የሙከራ በረራ አድርጓል፡፡
ይህ በቻይና አቪዬሽን ንግድ ኮርፖሬሽን የተመረተው አውሮፕላን በአለም ብቸኛ አውሮፕላን አምራቾቹን የአሜሪካውን ቦይንግ እና የአውሮፓውን ኤር ባስ እንደሚገዳደር ተመልክቷል፡፡
አውሮፕላኑ 164 መቀመጫ ያለው ሲሆን 130 ተሳፋሪዎችን ጭኖ የሶስት ሰአት የተሳካ የሙከራ በረራ አድርጓል ተብሏል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በአመት 150 አውሮፕላኖችን በማምረት ለአገር ውስጥ ፍላጎት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን ገና ወደ ገበያ ሳይገባ የ1ሺ 200 አውሮፕላኖች ግንባታ ትእዛዝ መቀበሉን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡
አውሮፕላኑ የቻይና ትልቁ የቴክኖሎጂ ውጤት ተደርጎም ተወስዷል፡፡
በተመሳሳይ ዜና ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቪል ሰዎችን ወደ ጠፈር መላክ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያደረገች ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ ሶስት ጠፈርተኞች ቲያንጎግ ወደ ተባለው የጠፈር ጣቢያዋ መላኳ ተገልጿል፡፡
“ሸንዙሀው ሚሽን 16” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይሄው የጠፈርተኞች ቡድን ዛሬ ማለዳ ላይ በተሳካ ሁኔታ ወደ ጠፈር ተልኳል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe