ቻይና ስድስተኛውን ትውልድ ወይም 6ጂ የተሰኘውን ኔትወርክ ማቅረብ የሚያስችል ሳተላይት ለሙከራ ማምጠቋን አስታውቃለች፡፡ ይህም ለቴክኖሎጂ እድገት በተለይ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፉ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
ቻይና ሞባይል በተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በኩል የመጠቀችው ይህች የኮሚዩንኬሽን ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ወደታችኛው የመሬት ምህዋር እንደገባች ሽንዋ ዘግቧል፡፡ በዚህም አስተማማኝ እና ያልተቆራረጠ የኢንተርኔት ግንኙነት ማቅረብ ያስችላታልም ተብሏል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የመጠቀችውን ሳተላይት መሰረት በማድረግ የስድስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት ኔትዎርክ ሙከራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡
የስድስተኛው ትውልድ የበይነመረብ አማራጭ እጅግ ፈጣን የሆነ ግንኙነት በማቅረብ ለተለያየ ዓላማ የሚውሉ ሰው አልባ በራሪ እና ተሽከርካሪዎች ፈጣን አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ በተጨማሪ የቁሶችን የኔትወርክ ግንነኙነት (IOT) ያሳልጣል።

