ቻይና በአንድ ጉዞ እስከ 10,800 ተሽከርካሪዎችን የማጓጓዝ አቅም ያለው ግሎቪስ ሊደር የተሰኘውን የዓለማችን ግዙፍ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ ገንብታ አስረክባለች።
መርከቧ በቻይና ስቴት ሺፕ ቢልዲንግ ኮርፖሬሽን ስር በሚገኘው ጓንግዙ ሺፕ ያርድ ኢንተርናሽናል የተገነባች ሲሆን፣ በጓንግዙ ከተማ ለደቡብ ኮሪያው ኤች.ኤም.ኤም (HMM) ኩባንያ ተላልፋለች።
ይህች 230 ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር ስፋት ያላት ግዙፍ መርከብ እንደ ተንሳፋፊ የመኪና ማቆሚያ ህንፃ የምታገለግል ሲሆን፣ ይህም የቻይናን እያደገ የመጣ የመርከብ ግንባታ አቅም በግልጽ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
መርከቧ የዓለም አቀፉን የባህር ላይ ድርጅት የታይር III የልቀት ደረጃን በሚያሟላ መልኩ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝና መደበኛ ነዳጅን የሚጠቀም ባለ ሁለት ነዳጅ ሞተር ሥርዓት ተገጥሞላታል።
መርከቧ በሰዓት እስከ 19 ኖትስ የመጓዝ ፍጥነትና 10.5 ሜትር ጥልቀት ያላት ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለረጅም ርቀት የመኪና ትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ ያደርጋታል።
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ቻይና በዓለም አቀፍ የባህር ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላትን ተጽዕኖ ይበልጥ እንደሚያሳድገው ተመላክቷል።//
ቻይና 10,800 ተሽከርካሪዎችን መጫን የሚችለውን የዓለማችን ግዙፍ መርከብ ገነባች

