ነዳጅ በርካሽ የሚሸጥባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

ሊቢያ ለዜጎቿ ነዳጅን በርካሽ ዋጋ በመሸጥ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 2ኛ ላይ ትገኛለች።

ሊቢያ አንድ ሊትር ቤንዚን 0.031 ዶላር (1 ብር ከ73 ሳንቲም) እንደምትሸጥም ተነግሯል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የቤንዚን ዋጋ የሚከታተለው ግሎባል ፔትሮል ፕራይስ በአዲሱ የፈረንጆቹ 2024 ዓመት የመጀመሪያ ወር ሀገራት ለዜጎቻው ነዳጅ የሚያቀርቡበትን ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ባወጣው መረጃ መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ አንድ ሊትር ነዳጅ በአማካይ 1.30 ዶላር (72 ብር ከ72 ሳንቲም) በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ሆኖም ግን አንዳንድ ሀገራት ከተቀመጠው ከአማካይ ዋጋ ከፍ ባለ ዋጋ የሚሸጡ ሲሆን፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ዝቅ ባለ ዋጋ እንደሚሸጡም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።

በዚህም መሰረት ሊቢያ ለዜጎቿ ነዳጅን በርካሽ ዋጋ በመሸጥ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 2ኛ ላይ ትገኛለች የተባለ ሲሆን፤ አንድ ሊትር ቤንዚን 0.031 ዶላር (1 ብር ከ73 ሳንቲም) እንደምትሸጥም ተነግሯል
ከሊቢያ በመቀጠልም አልጄሪያ አንድ ሊትር ቤንዚን አልጄሪያ 0.342 ዶላር (19 ብር ከ13 ሳንቲም) በመሸጥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፤ አንጎላ 0.362 ዶላር (20 ብር ከ25 ሳንቲም) በመሸጥ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።

ግብጽ 0.403 ዶላር (22 ብር ከ54 ሳንቲም) እንዲሁም ሱዳን 0.700 ዶላር (39 ብር ከ16 ሳንቲም) በመሸጥ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ነዳጅ በርካሽ የሚሸጥባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝርን ከላይ በምስል ተቀምጧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe