ናይጀሪያዊቷ ኢውያላ የመጀመሪያዋ ሴትና አፍሪካዊ የአለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆኑ

ናይጀሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ የመጀመሪያ ሴትና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ የአለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል።

የአዲሷ ናይጀሪያዊት የአለም ንግድ ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተርነት ሹመት የፀደቀው የድርጅቱ አጠቃላይ ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ አድርጓ ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ነው።

የቀድሞ የናይጀሪያ የገንዘብ ሚኒስቴር ዶክተር  ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ የአለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርም ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነት እንዳላቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

የአለም ንግድ ድርጅት በአሁን ወቅት በሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግጭት፣ ሀገራት እርስ በርሳቸው ታሪፍ መጣላቸው እና  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው የኢኮኖሚ ችግር መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚገቡ ፊት ለፊቱ የተደቀኑ ተግዳሮቶች መሆናቸው ይነገራል።

አንድንድ ተንታኞችም የአለም ንግድ ድርጅት በአሁን ወቅት ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ይናገራሉ።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe