ንጉሱ ጥላሁን የሽመልስ አብዲሳን ንግግር ተቹ

የአቶ ሽመልስ ንግግር የሰማሁት በትናንትናው እለት በባህርዳር እያለሁ ነው እናም ይህን ንግግር በሁለት መልክ ማየት እፈልጋለሁ። የለውጡን አነሳስና የለውጡን ሂደት ለውጡን የሚያይበት አተያይ ትክክል አይደለም፤ ስህተት ነው የሚል ሃሳብ አለኝ።

ለውጡ የመጣው በሁሉም ፍላጎትና ተሳትፎ በተለይም ደግሞ በወቅቱ የኦህዲድና የብአዴን አመራሮች ጥምረት እንዲሁም በኦሮሞና አማራ ህዝቦች ትግል በሌሎችም ብሄር ብሄረስብ ህዝቦች ግፊት ነው።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ፍላጎት፣ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ለመመለስ ከለውጡ በፊት የተነሱ አንኳር ጥያቄዎች ለውጡን የግድ ያሉት አንኳር ጥያቄዎች የሁላችንም ጥያቄዎች ስለነበሩ በሁሉም ረገድ ለውጡን የግድ ያሉት መገፋቶች ሁሉንም የገፉ ስለነበሩ፡ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ቤተኛና አልፎ ሂያጅ የሌለባት ኢትዮጵያን ለመገንባት፡ ፍትሃዊነትን እኩልነትን አላማው ያደረገ ህብረ ብሄራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ ትግል የተደረገበት እንጂ ከየትኛውም ወገን በተናጠል ከፍተኛ ሚዛን የወሰደበት ትግል አልነበረም። እኩል ርብርብ የተደረገበት የሚናና የቦታ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በመናበብ የመጣ ለውጥ ነው።

በኦሮሚያም የነበረው የትግል መነሻ ይኸው ነው። አንድነት ነው፣ አብሮነት ነው። ኦሮሚያም ደግሞ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ እንድትሆን ነው። እኩልነት የተረጋገጠባት እንድትሆን ነው። በባህሪውም እሳቸውም ሲገልፁት እንደነበረው አቃፊና ደጋፊ ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲሉ እንደነበረው ይህንን በአንድነት የመኖርን አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን በአንድነት የመገንባት ሃሳብን ያጠነጠነ ለውጥ ነው። ከዚህ ለውጥ የገቀዳው ለውጡ የወለደ የፓርቲያችንም ውህደት ይህንኑ ማእከል ያደረገ ነው።

የፓርቲያችንም መስመር የሚመራበት የመደመር አስተሳሰብ እሳቤ የሚነሳው ከአንድ ብሄር ከአንድ ማንነት ሳይሆን ከሰው ልጅ ነው የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው። ኢትዮጵያ ለሰው ልጆች ሁሉ እኩል የምትሆንበት አብረን የምናድግበትና የምንበለፅግበት የአንዱ ባይተዋር ሌላኛው ቤተኛ የማይሆንበት ኢትዮጵያ መገንባት የሚል ሃሳብ ያነገበ ለውጥ ነው ስለዚህ ከነዚህ መመዘኛዎች አኳያ ሳየው በርካታ ስህተቶች ያሉበት ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
…..
ጥያቄ. .. በሁለቱ ፓርቲዎች መሃል መሻከርን ሊፈጥር ይችላል ሃገሪቷንም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ነገር ይሰማልና እንደዛ አይነት ነገር ሊኖር ይችላል?

መልስ:- በመጀመሪያ ደረጃ ብልፅግና የሁለቱ ወይንም የሶስት ፓርቲዎች አይደለም። ብልፅግና የመላ ኢትዮጵያውያንና ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈና ያሳተፈ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፡ ከምእራብ እስከ ምስራቅ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ትናንትና ባይተዋር ሆነው ተገፍተው የነበሩ ብሄር ብሄረሰቦችም ነው ስለ አጠቃላይ ሃገራዊ ሁኔታ ስንነጋገርም የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ነው ኢትዮጵያ ለሁሉም የምትመች አድርገን የምንሰራት ሃገር ትሆናለች ስንል 86 ቱን ብሄር ብሄረሰቦች የሚመለከት ነው።

በምንም መልኩ ግን ከተረጋጋን ከሰከንን በማንኛውም ሂደት ስህተት ይፈፀማል። ማንም አካል ከስህተቱ ሊማር ይችላል። ትግል ያድናል፡ ይህንን ሃገር የሚያድነው ትግል ነው። አመራሩ ይታገላል አመራሩ ይታረማል የሚሻሻለው ይሳሻላል በመሆኑም ኢትዮጵያ ከያንዳንዳችን በላይ የኢትዮጵያ ህዝቦችም ከያንዳንዳችን አመራሮች በላይ ስለሆኑ እኛ አመራሮች በምንሰራው ስህተት ህዝብና ሃገር አይፈርስም ህዝብ ግጭትም አይፈጠርም ግን ደግሞ ይህን ስም ብሎ መናገር ሳይሆን ማስተዋል መረጋጋት ከስህተት መማር ይጠበቃል።

(አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠ/ሚኒስትር ቢሮ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ሃላፊ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ክልል ኘረዝደንት አወዛጋቢ ንግግርን አስመልክቶ በኢሳት ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ )

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe