ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  የ 830 ጫት ላኪ ድርጅቶችን ፈቃድ ሰረዘ፣ 

ንግድ ሚኒስቴር መንግስት  ከጫት ምርት የሚያገኘውን ገቢ ለማሳደግ እና ህጋዊ  ስርአትን ለማስፈን  የኮንትሮባንድ ንግድን  ለመከላከል አስተማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን አስታውቋል፤

ሚኒስቴሩ  እርምጃ የወሰደው በህገ-ወጥ ተግባራቱ ላይ ተሳትፎ አላቸው ባላቸው ድርጅቶች ላይ ሲሆን በተለይም ህጋዊውን አሰራር ወደ ጎን በመተው የንግድ ፈቃድን  ሳያሳድሱ ምርት ወደ ውጪ የላኩ እና ላልተገባ አገልግሎት ያዋሉ 830 ጫት ላኪ ድርጅቶች ላይ መሆኑ ተመልክቷል፤

ድርጅቶቹ የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ የጫት ምርት ሲልኩ የተገኙ እንዲሁም የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ኖሯቸዉ በህገ ወጥ መንገድ የምርት መላኪያ ፍቃድ ለሶሰተኛ ወገን አሳልፈዉ የሰጡ ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡

የጫት ንግድ  ህገ-ወጥነት አስከፊ ገጽታ እየተላበሰ መምጣቱን የሚገልፅው ሚኒስቴሩ መንግስት ከጫት ንግድ  ማግኘት የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ ከማሳጣቱም ባሻገር የሀገርን ሀብት ለጎረቤት ሃገራት ሲሳይ በማድረግ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል ብሏል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe