አልጄርያ የ14 የአፍሪቃ ሃገራት 1ቢሊየን ዶላር እዳ ሰረዘች

የሰሜናዊ አፍሪቃዊቷ አልጄርያ በአህጉሪቱ ያላትን ሚና ለማሳደግ የአፍሪካ ወንድሞችን እዳ ሰርዣለሁ ብላለች፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ራምታኔ ላማምራ ስማቸውን በዝርዝር ባያስቀምጡም ለ14 ሃገራት 1ቢሊየን ዶላር እርዳታ መንግስታቸው መሰረዙን ለራዲዮ ፍራንስ አስታውቀዋል፡፡

አለምን አንድ ማድረግ አለብን፣ ለዚህ መነሻችን ደግሞ በአፍሪቃ ያለንን ስፍራ ማሳደግ ነው ያሉት ሚንስትሩ አልጄርያ በአፍሪቃና አለም ለውጥ ላይ ያላትን በጎ ሚና መጨመር ትፈልጋለች ብለዋል፡፡ ሚንስትሩ በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ጉብኝት እያደረጉም ነው፡፡

በነገራችን ላይ አልጄርያ ነዳጅ ዘይት፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የነዳጅ ውጤቶችን የምታመርት የአፍሪቃ አራተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ናት፡፡ (በጥቅል የሃገር ውስጥ ምርት በቅደም ተከተል ናይጄርያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄርያ፣ ሞሮኮ ቀዳሚ ናቸው፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe