አማርኛ ከአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋዎች አንዱ እንዲሆን ኢትዮጵያ ሀሳብ አቀረበች

ዛሬ በተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ይህን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬ 61 አመት ሲቋቋም የመመስረቻ ሰነዱ ከተፈረመባቸው አራት ቋንቋዎች አማርኛ አንዱ እንደነበር አስታውሰዋል።

አክለውም የአማርኛ ቋንቋ በህብረቱ ውስጥ መካተት የቋንቋ ብዝሀነትን እንደሚያሰፍን ጠቁመዋል።

በአሁን ወቅት የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋዎች አረብኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፖርቹጊዝ፣ ስፓኒሽ እና ኪስዋሂሊ ናቸው። በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ በስፋት የሚነገረው ኪስዋሂሊ የተካተተው የዛሬ ሁለት አመት ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe