አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢራን ላይ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን ልትጠቀም ከጫፍ ደርሳለች ተባለ

የዩኤስ ሴንተራል ኮማንድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን ለማሰማራት ጥያቄ ማቅረቡን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በጦርነት ቀጠና ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ስታሰማራ የመጀመሪያዋ ይሆናል ተብሏል፡፡

በኢራን ላይ በሚደረገው ዘመቻ ብላክ ኢግል የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ጦር መሳሪያዎችን ለመጠቀም እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልተላለፍ የዜና ምንጩ አስታውቋል፡፡

እስካሁን በጦርነቱ በኢራን በኩል ከ3ሺ በላይ ሰዎች ሲገደሉ፤አሜሪካ ደግሞ ወደ 400 የሚደርሱ ወታደሮቿ ቆስለውባት እንዲሁም ከ10 ያላነሱት ደግሞ ተገድለውባታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን እጅ እንድትሰጥ ጠየቁ፡፡

ትራምፕ ዋሽንግተን በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችው እገዳ ስኬታማ መሆኑን አንስተው፤በሆርሙዝ ሰርጥ ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት ቴህራን እጅ እንድትሰጥ አሳስበዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ ለዚህ ለፕሬዝዳንቱ ንግግር ጠንካራ ምላሽ የሰጠች ሲሆን፤የፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ የአሜሪካ ዘመቻ ውጤታማ ያልሆነ በማለት አጣጥለውታል፡፡

ከዚህ ባለፈ የሀገሪቱ ጦር ሃይል እስካሁን ያሳየው ትዕግስት ለዲፕሎማሲ ዕድል ለመስጠት የታሰበ መሆኑን በመግለጽ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ፑቲን አቻቸው ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት እንዳይከፍቱ አስጠንቅቀዋል፡፡ ሁለቱም መሪዎች በስልክ ባደረጉት ንግግር ትራምፕ የተኩስ አቁምን እንዲራዘም ማድረጋቸው ትክክለኛ ውሳኔ እንደነበር ፑቲን መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

ከዚህ ባለፈ መሪዎቹ በዩክሬን ጉዳይም ስለ መምከራቸው ተሰምቷል፡፡ የስልክ ንግግሩ ወደ 90 ደቂቃ ያህል ነበር የተባለ ሲሆን፤ትራምፕ ንግግራችን ጥሩ ነበር ብለዋል፡፡

ሞስኮ በዚህ ጦርነት ለኢራን የስለላ መረጃዎችን ትሰጣለች በሚል ስሟ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡//

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe