አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ እንዳትመታ ሩሲያ አስጠነቀቀች

አሜሪካ በሩሲያ በተገነባው የኢራን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ላይ የምትፈጽመው ማንኛውም ጥቃት “ሊጠገን የማይችል” መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል ሞስኮ አስጠንቅቃለች።
የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዛሬ በሰጡበት መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥ የማይከፈት ከሆነ የኢራንን የኒውክሌር ማመንጫዎች “እንደሚያወድሙ” ስለመዛታቸው እንደተጠየቁ የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ቃል አቀባዩ ምላሽ ሲሰጡ “አስከፊ በሚባል ደረጃ የተወጠረው” የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ ሊፈታ የሚችለው በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮች ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
ፔስኮቭ አክለውም፤ በኒውክሌር ተቋማት ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት “እጅግ አደገኛ እንዲሁም ሊጠገን በማይችል መዘዝ የተሞላ” እንደሚሆን ገልጸዋል። ሩሲያ ይህንን በተመለከተ “ተገቢ የሆኑ መልዕክቶችን” ለአሜሪካ ማስተላለፏንም ጠቅሰዋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe