አሜሪካ የኢራንን የዩራኒየም ክምችት ወደ ሩሲያ ለማዛወር የቀረበውን የክሪሚሊን የውሳኔ ሃሳብን ውድቅ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
ክሪሚሊን ሩሲያ የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም ለመውሰድ ማሰቧ ጥሩ መፍትሔ ነው ብሏል፡፡ የክሪሚሊን ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ግጭት ለመፍታት እንዲረዳ በሚል በኢራን እጅ የሚገኘውን የበለጸገ ዩራኒየም ክምችት ለመውሰድ አቅዳለች፡፡
ዩናይትድስቴትስ ሩሲያ ሁሉንም የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም በመውሰድ የመካከለኛው ምስራቅን ግጭት ለመፍታት ያቀረበችውን ሃሳብ ውድቅ ማደረጓን ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት፡፡
ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሰኔ ወር ነበር የኢራንን የተከማቸ ዩራኒየም ለመረከብ እቅድ ያቀረበችው ተብሏል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነት ተግባራዊ እርምጃ አልተወሰደም፡፡
ሰሞኑን በወጡ ሪፖርቶች መሠረት ሩሲያ እቅዱን በዚህ ሳምንት ነው ዳግም ያቀረበችው፡፡ የሩሲያ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን መግለጻን አንስተዋል፡፡
ይህ ደግሞ ጥሩ መፍትሔ ቢሆንም እስካሁን ግን በአሜሪካኖች በኩል ውድቅ ተደርጓል ብለዋል፡፡//

