አሜሪካ የጦር መሳሪያ የጫኑ መርከቦችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አስጠጋች

ዩናይትድ ስቴትስ የጦር መሳሪያ የ የጫኑ መርከቦችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ማስጠጋቷ ተገልጿል።

የትራምፕ አስተዳደር የጦር መሳሪያ እና የሰለጠኑ ወታደሮች የያዙ መርከቦችን ወደ  መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መላካቸውን የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አስታውቀዋል።

መርከቦቹ የተላኩበት ዋና አላማም ኢራን በቀጠናው ለምታደርገው ትንኮሳ ግልፅና ቀጥተኛ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ኢራን በአሜሪካ እና አጋር ሀገራት  ላይ ለምታስተላልፈው ዛቻና ማስፈራሪያ አፀፋዊ ምላሽ መሆኑ ነው የተገለፀው።

አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦር የመማዘዝ አቅድ የላትም ያሉት ጆን ቦልተን፥  ሀገሪቱ ፊት ለፊትም ሆነ በእጅ አዙር በአሜሪካ እና አጋር ሀገራት ላይ ለምትፈፅመው ጥቃት አፃፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ግን ዝግጁ ነን ብለዋል።

ወደ ስፍራው ያቀኑት ወታደሮችም በማንኛውም ጊዜ ለሚደረግ ትንኮሳ የማያዳግም እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ነው ጆን ቦልተን የገለጹት።

በቅርቡ አሜሪካ የኢራን አብዮት  ዘብ ጠባቂ ወታደሮችን በአሸባሪነት መፈረጇንና በተመሳሳይ ኢራን በሩቅ ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በአሸባሪነት መፈረጇን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መላከል ውጥረት መንገሱ ይታወቃል።

ምንጭ፡ ቢቢሲ ጠቅሶ ፋና ቢሲ ዘግቦታል

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe