አሜሪካ 500 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባች እንደሆነ ፕሬዜዳንቷ ገልፀዋል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደራቸው በመላ አገሪቱ 500,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሆነ አሳውቀዋል።

በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀገሪቱም ይህንን በእጅጉ እያበረታታች ነው።

በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የሚሽከረከሩ የኤሌክትሪ መኪናዎች ከዓመት ወደ ዓመት እጅግ በጣም ፈጣን የሚባል ባይሆንም እድገት እያሳዩ ይገኛል። የመኪና አምራቾችም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተያየ ሞዴል እያመረቱት ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና እየጨመሩ ይገኛሉ።

አሜሪካ በ2050 ከካርቦን-ነፃ እንድትሆን አሽከርካሪዎች በነዳጅ ኃይል ከሚሰሩ ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ታምናለች።

የአሁኑ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በ2030 ከአዳዲስ የመኪና ሽያጭ ግማሹ የኤሌክትሪክ ፣ ወይም ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ትልቅ ግብ የወጠኑ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2030 ግማሹ ኤሌክትሪክ ከሆኑ፣ በ2050 በአሜሪካ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መኪኖች ከ60-70 በመቶ የኤሌክትሪክ / ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ሊሸፍኑ ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe