አርሰናል ለሦስተኛ ጊዜ የካራባኦ ዋንጫን ለማሳካት በመጪው እሁድ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ይፋለማል

 አርሰናል ለአራት ዋንጫዎች እያደረገ ባለው ጉዞ የመጀመሪያ ፈተናውን በመጪው እሁድ በካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በ9 ነጥብ በመብለጥ እየመራ የሚገኘው አርሰናል በካራባኦ ካፕ የፍጻሜ ፍልሚያ የሚጠብቀው ሲሆን፥ በሻምፒየንስ ሊግ እና ኤፍ ኤ ካፕ ለሩብ ፍጻሜ ማለፍ ችሏል፡፡
የሚኬል አርቴታው ቡድን ከ22 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የሊጉን ዋንጫ ለማሳካት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የተቃረበ ሲሆን፥ በሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ይጠብቀዋል፡፡
አርሰናል በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከሻምፒየንሺፑ ክለብ ሳውዛምፕተን ጋር መደልደሉም አይዘነጋም፡፡
መድፈኞቹ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን እንዲሁም በታሪካቸው ለሦስተኛ ጊዜ የካራባኦ ዋንጫን ለማሳካት በመጪው እሁድ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በዌምብሌይ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የፍጻሜ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
በዚህም የሰሜን ለንደኑ ክለብ በመጪው እሁድ በሚያደርገው ጨዋታ የአራት ዋንጫዎች (ኳድራፕል) ጉዞውን በድል ይጀምር ይሆን የሚለው ከወዲሁ ይጠበቃል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe