በተለየ ሁኔታ መስራት ያልፈለጉ ከሌሉ በቀር ለሁሉም አርቲስቶች ጥሪ ተደርጓል ተብሏል
የአራት ትውልድ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከማህሙድ አህምድ እስከ ፀሀዬ ዮሃንስና ፍቅረ አዲስ ነቃጥበብ ፤ ከህብስት ጥሩነህ እስከ ራሔል ጌቱ ና ዳዊት ፅጌ የሚጣመሩበትና በአንድነት የመቆምን አስፈላጊነት ያሳያል የተባለ “ዛሬም ለኢትዮጵያችን” የተሰኘ ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ።
ይህም ታላቅ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ድግስ የፊታችን ጥር 21 ቀን 2014 በመስቀል አደባባይ የሚከናወን ሲሆን፤ በተጨማሪም በወዳጅነት ፓርክ ጥር 19 ቀን 2014 ሰሞኑን ወደሀገራቸው እየገቡ ላሉ ዲያስፖራዎች እንደሚደረግ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።
በማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለቻ ላይ የኪነጥበባ ባለሙያዎቹ አስተባባሪ አርቲስት ታማኝ በየነ እንደተናገረው ዛሬ የተሰባሰብነው ነገ ደግሞ የሙዚቃ ኮንሰርት የምናቀርበው ሀገራችን ከመፍረስ ስለዳነች ነው ብሏል፤
የተሰባሰብንበት ዋና ኣከላማ ኢትጵያ ትፈርሳለች ብለው ለተነሱት ሃይሎች ኢትዮጵያ እስትንፋሳችን ነች አትፈርስም የሚለውን መልዕክት ማስተላላፍ ነው ያለው አርቲስት ፀጋዬ እሸቱ እንደማንኛውም ዜጋ ለሀገራችን ማድረግ ያለነብንን ነገር እናደርጋለን ብሏ፡፡
ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በተላያየ ጊዜ ሀገራችን ችግር ላይ በገባችበት መበማንኛውም ወቅት ከህዝባቸው ጎን በመቆም በሙያቸው አስተዋእ ሲያደፍጉ እንደነበረር የታገረው ታማኝ አሁንም ኢትዮጵያና ህዝቧ በችግር ላይ ባላበት ወቀወውት በሙያቸው አስተዋፆኦ እንዲያደርጉ ለሁሉም አርቲስቶች ጥሪ ተደርጓል፤በተለየ ሁኔታ መምስራት ያልፈለገ አርቲስት ከሌለ በቀር ለሁሉም ጥሪ ተደርጓል ያልሰሙም ካሉ አሁን በመገናኛ ብዙሃን በድጋሚ ጥሪያችን እናቀርባለን ብሏል፤
የሙዚቃ ዝግጅቱ ሙሉ ገቢው በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት የሚሰጥ ሲሆን፤ በየነ መላው አገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ትኬት በመግዛት አላማውን እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል። የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትም ይኖረዋል ተብሏል፤
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ታማኝ ሚዲያ ሲሆን፣ በሙዚቃ ድግሱ አርቲስት መሀሙድ አህመድ፣ ፀሃዬ ዬሀንስ፣ ህብስት ጥሩነህ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ጸጋዬ እሸቱ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ታደለ ሮባ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ያሬድ ነጉና ዳዊት ጽጌን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
የመዚቃ ድግሱ የትኬት ዋጋ ገና እስከአሁን እንዳልተወሰነ የተገለፀ ሲሆን፤ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም አርቲስት ታማኝ በየነ በመድረኩ ተናግሯል።
በተጨማሪም በመላው የአለም ክፍል የሚገኙና የሙዚቃውን ድግስ በአካል ለመታደም ለማይችሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የኦን ላይን ትኬት ሽያጭ እንደሚከናወን እና ሙሉ ፕሮግራሙን በኦን ላይ መታደም እንደሚችሉም ተገልጿል።
አርቲስቶቹ በሙያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ በአፋር ክልል የወደመውን ሆስፒታል በተሻለ መልኩ ገንብተው በጥላሁን ገሠሠ ስም የመሰየም እቅድ መኖሩ ተነግሯል፤

