አርቲስት ሰላም ተስፋዬ የቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ ምርት ለማስተዋወቅ የአንድ ዓመት ውል ተፈራረመች

ቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ ከ27 አመታት በላይ ምርቶቹን በጥራት ለደንበኞቹ በማድረስ የሚታወቅ ሲሆን ድርጅቱ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ብራንድ አምባሳደር
ለመሆን አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ፈርማለች።
አርቲስቷ ለአንድ ዓመት በሚያቆያት በዚህ የአምባሳደርነት ስራዋ ምን ያክል ክፍያ እንደተከፈላት ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቢቀርብላትም ምላሽ ሳትሰጥ አልፋለች።
ቀስተ ደመና ሁሉም የፍራሽ ምርቶቹ በከፍተኛ ደረጃ ጥራታቸውን በጠበቀ ሁኔታ መመረታቸውንና ምንም አይነት ለጤና ጎጂ የሆኑ የማምረቻ ኬሚካሎችን የማይጠቀም መሆኑ የሚለየው ሲሆን ለዚህም ከተለያዮ አለም አቀፍ እውቅና ያገኘ መሆኑን የቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ይሄዴጎ አቢሴሎም በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ገልጸዋል።
ቀስተ ደመና ከሚታወቅበት የስፖንጅ ፋብሪካ ባሻገር በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ “ ኬኔትክ ዳውን መልቲሚዲያ ” እና “ድንቅ ቴሌቪዥን” የተሰኙ ሁለት እህት ኩባንያዎች አስተዋውቋል።
ድንቅ ቴሌቭዥን በቅርብ ጊዜ አየር ላይ ለመዋል የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ ይገኛልም ተብሏል።
በሀገራችን በመዝናኛ ኢንደስትሪ የሚዲያ ዘርፈ የተለየ ነገርን ይዞ ይመጣል የተባለው ድንቅ ቲቪ ኢትዮጲያን በዓለም የማስተዋወቅ ራዕይ እንዳለውም ተገልዖዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe