አርቲስት አብርሃም ወልዴ ሊሞሸር ነው፤

የሠርጉን ወጪ ለተፈናቃይ ወገኖች አውላለሁ  ብሏል

አንጋፋው አርቲስት አብርሃም ወ፤ልዴ ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛው ጋር ሊሞሸር መሆኑን ገልጦ ለሠርግ ስነስርዓቱ የመደብውን ወጪ እንዲሁም ከወዳጅ ዘመዶቹ የሚበረከትለን ስጦታ አካቶ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ለተፈላቀሉ ወገኖቹ መርጃ እንደሚያውለው በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ አድርጓል፤

አብርሃም ለዚሁ ብሎ በውጭ ሀገር ያሉ ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ  በጎፈንድሚ አማካይነት ገንዘብ ለማሰባሰብ ዘመቻ የጀመረ ሲሆን ግቡን 50 ሺ ብር አድርጎ የጀመረ ሲሆን በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ8 ሺ በዶላር በላይ ድጋፍ ማግኘቱ ታውቋል፤

አብርሃም ይህኑን የገቢ ማሰባሰቢያ አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው መልዕክት የሚከተለው ነው፡፡

በሃገራችን፡ “ሰርግና፡ ሞት፡ አንድ፡ ነው” ይባላል። በሞት፡ ሃዘንም፡ በጋብቻ፡ ሰርግም፡ እኩል፡ ቦታ፡ ይሰጣቸዋል። እኔ፡ ግን፡ ጋብቻ፡ ለሃገሬ፡ ከመስራት፡ እና፡ ከመሮጥ፡ የሚያሰናክለኝ፡ ብወልድ፡ ደግሞ፡ ፈሪ፡ ሆኜ፡ እንደ፡ ልቤ፡ እንዳልናገር፡ የሚያደርገኝ፡ ስለሚመስለኝ፡ ብቻ፡ ለዓመታት፡ ስሸሸው፡ ኖርያለሁ። አሁን፡ ግን፡ ግዜው፡ ሲገፋ ሃሳቤን፡ አስቀይሮኝ፡ ወደ፡ ትዳር፡ አለም፡ ልገባ፡ ነው።

እድሜውን፡ ሙሉ፡ ስለ፡ ሃገርና፡ ስለ፡ ህዝብ፡ ብቻ፡ አስቦ፡ ለኖረ፡ ሰው፡ ምናልባት፡ ሃዘኑን፡ እንጂ፡ ሰርጉን፡ ብቻውን፡ ሊያደርገው፡ እንዴት፡ ይቻለው፡ ይሆን? ስለዚህም፡ እኔና፡ የህይወት-አጋሬ፡ የደስታችን፡ ተካፋይ፡ መሆን፡ ለምትሹ፡ ወዳጆቻችን፡ ሁሉ፡ በመንፈስ፡ ከእኛ፡ ጋር፡ እንደምትሆኑ፡ በፅኑ፡ ልብ፡ በማመን፡ የሰርጋችን፡ ጥሪ፡ በያላችሁበት፡ ይድረሳችሁ፡ እንላለን።

ከቤተሰቦቻችንና፡ ከቅርብ፡ ጓደኞቻችን፡ አንስቶ፡ ለሰርጋችሁ፡ ምን፡ እናድርግላችሁ፡ እያላችሁ፡ የጠየቃችሁን፡ እና፡ ለማድረግም፡ ለምትሹ፡ ወዳጆቻችን፡ እና፡ አክባሪዎቻችን፡ ሁሉ፡ ለእኛ፡ ልታደርጉ፡ የምትፈልጉትን፡ ሁሉ፡ በጦርነቱ፡ ለተፈናቀሉና፡ ለተጎዱ፡ ወገኖቻችን፡ ድጋፍ፡ እንዲሆንልን፡ ስንል፡ የጎፈንድሚ፡ አካውንት፡ከፍተናልና፡ ድጋፋችሁን፡ እንድታሳዩንና፡ እንድትተባበሩን፡ ስንል፡ በኢትዮጽያዊ፡ እህታዊና፡ ወንድማዊ፡ ፍቅርና፡ አክብሮት፡ እንጠይቃችኋለን።
ይህንንም፡ ፈለግ፡ ሌሎች፡ ሰርገኞች፡ ሁሉ፡ እንዲከተሉት፡ የእግዚአብሔር፡ ፍቃድ፡ ይሁን።

ሰርግና፡ ሞት፡ አንድ፡ ነው። በደስታም፡ በሃዘንም፡ መረዳዳት፡ ኢትዮጵያዊው፡ ህይወታችን፡ ነው።

ምንም፡ እንኴን፡ በአሁኑ፡ ሰዓት፡ ሃገራችን፡ ምጥ፡ ላይ፡ ብትሆንም፡ እንድነቷንና፡ ሰላሟን፡ ወልዳ፡ ዳግም፡ ታላቅነቷን፡ እንደምትጎናፀፍ፡ ጥርጥር፡ የለንም። ሰርጋችንም፡ የነገዪቱ፡ ኢትዮጵያችን፡ አንዱ፡ የተስፋና፡ የብሩህ፡ ቀን፡ ምልክት፡ እንዲሆንልን፡ እንመኛለን።

አብርሃም፡ ወልዴ፡ እና፡ የህይወት፡ ጓደኛዬ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe