አርቲስት ፍቅሩ ተሰማ (ካሥማሠ) የጆኒ ዎከር አለማቀፍ አርቲስቶች ስብስብን ተቀላቀለ

በኢትዮጵያ የሂፕ ሆፕ የሙዚቃ ስልት አቀንቃኝ አርቲስት ፍቅሩ ተሰማ (ካሥማሠ) የጆኒ ዎከር አምባሳደር በመሆን አለማቀፍ አርቲስቶች ስብስብን ተቀላቀለ።

በዚህ ስብስብ ውስጥ ኢትዮጵያዊው አርቲስት ሳሚ ዳንን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካውያን ሙዚቀኞችና የመዚቃ ፕሮዲውሰሮች የሚገኙበት ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አይቮሪያዊው ዲዲ ቢ እንዲሁም ዛምቢያዊቷ ክሊኦ አይስክዊን ይገኙበታል፡፡

ካሥማሠ በአዲሱ የአጋርነት ስምምነት መሰረት ለአድናቂዎቹ አዳዲስ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን፣ የአልበም ምረቃዎችን እና በመጪዎቹ ወራት ልዩ ልዩ ትርኢቶችን ሊያቀርብም ተሰምቷል።

“በሙያዬ ውስጥ በጣም አስደሳቹ እና በግሌ ደግሞ ደፋር እርምጃ የወሰድኩበት ጊዜ ነው።” በቅርቡ ለህዝብ የሚደርሱ በርካታ አዳዲስ ሥራዎች አሉኝ። እኔ ሁሌም ለአድናቂዎቼ ምርጥ ምርጡን ለማቅረብ እተጋለሁ።” ያለው ካስማሠ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከታዋቂ አርቲስቶች ጋር በመተባበር ከሚታወቁ ጆኒ ዎከር ካሉ ታዋቂ የንግድ ምልክቶች ጋር መተባበሩም፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሚገኝ እናዳረጋገጠለት ተናግሯል።

የጆኒዎከርና ሪዘርቭ ከፍተኛ የብራንድ ሥራ አስኪያጅ፤ ያምባወርቅ ማይረጉ በበኩላቸው የካሥማሠን ሚና ሲገልጹ፤ ”ካሥማሠ በግሉ የወሰዳቸውን ዋና ዋና ርምጃዎች እና የአርቲስቱ የፈጠራ ሃይል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የፈጠረውን መነቃቃት ለማድነቅ እንወዳለን፡፡” ያሉ ሲሆን፤ ካሥማሠ በተሰጥኦና ለራስ ታማኝ ቀመሆን ምንም ነገር ማድረግ እንደሚቻል ያስተማረን አርቲስት ነው ብለዋል፡፡

በ2020 ቀዳሚውን “ማለዳ” አልበሙን እንደለቀቀ በ18 ወራት ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለው ካሥማሠ፤ በዚህ ዓመት “ባህል ወግ” የተሰኘውን የመጀመሪያ ሙሉ የስቱዲዮ አልበም ከዓለም ዓቀፍ የሙዚቃ ባለሙያ አንጋፋው የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ የቦብ ማርሌ ልጅ ጁሊያን ማርሌ ጋር ለህዝብ ያደረሰ ሲሆን፤ በተጨማሪም ከሁለት ጊዜ የግራሚ እጩ ፕሮቴጄ ጋር “መላ መላ” የተሰኘውን ነጠላ ዜማውን በድጋሚ ለህዝብ ማድረሱም ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe