አርቲስቶቹ ‹አምባሳደሮች› ‹አርቲስቶችን ለንግድ አሻሻጭነት የመምረጥ ግልፅነት የት ድረስ ነው ?›

ገበያ ቀዝቀዝ ሲል የሸማቾችንና የገበያተኛውን ቀልብ ሊስብ የሚችል መንገድ ማፈላለግ የተለመደ የገበያ ሙያተኞች ስልት ነው፤ በህዝብ ዘንድ መልካም ስምና ዝና ያላቸውን ታዋቂ ሰዎች አግባብቶ አሳምኖና አልፎ አልፎም ተደራድሮ የተቀዛቀዘውን ገበያ ማነቃቃት ጊዜ ያለፈበት ዘዴ ተደርጎ አይቆጠርም፤ ለዚህም ይመስላል በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ሪል ስቴቶች የፋይናንስ ተቀማትና ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ሳይቀሩ ታዋቂ ያሏቸው ሰዎችን በማግባባት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርገው ‹ሰየሙ› የሚለው ዜና በስፋት ሲናፈስ የሚሰማው፤

ታዋቂ ሰዎችን ለአንድ ምርት ወይም አገልግሎት መለያ ምልክት አድርጎ የመሰየም ጠቀሜታ ከብዙ አቅጣጫ የሚታይ ነው፤ በተለይም አርቲስቶችን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየም አርቲስቶቹ በሙያቸው ያገኙዋቸውንና የገነባቸውን መልካም ስምና ዝና መሰረት በማድርግ እንዲተዋወቀ የተፈለገውን ምርት ወይም አገልግሎት በቀላሉ ገበያ ውስጥ ለማስገባት ያግዛል፤ 

የአርቲስቶቹ አድናቂዎችና የሙያው ተከታዮችም የገበያ ተጽእኖ ውስጥ ወድቆ የነበረን ምርት በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ በማድረግ በኩል የአርቲስቶቹን ሚና የላቀ ያደርገዋል፤ በበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት የሚሰየሙ አርቲስቶቸና ታዋቂ ሰዎች የሚያስተዋውቁትን ምርት ወይም አገልግሎት በሸማቹ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ በበጎ አይን እንዲታይ ከማድረግ በተጨማሪ በግል ህይወታቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ጥቅም ያገኙበታል፤ በእርግጥ አርቲስቶቹ በብራንድ አምባሳደርነት ከአንድ ድርጅት ጋር ተስማምተው ስምምነታቸውን ይፋ ሲያደረጉ የሚያገኙት ጥቅማ ጥቅም በግልጽ ባይገለጽም ብዙ ጊዜ በገንዘብ አልፎ አልፎም በአይነት የጥቅም ተጋሪ የሚሆኑበት ሁኔታ አለ፤

የፋብሪካ ወይም የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማስተዋወቅ የሚዋዋሉ አርቲስቶች በግል ህይወታቸው ሳይቅር ያንን የሚያስተዋውቁትን ምርት እንዲጠቅሙ ሲገደዱ እንደ ሪል ስቴት ያሉ ግንባታዎችን የሚያስተዋውቁት ደግሞ ነጻ ወይም እጅግ አነስተኛ ሊባል በሚችል ዋጋ የቤት ባለቤት ሊሆኑ የሚችሉበት እድል አለ፤ በሌላ በኩል በክብር አምባሳደርነታቸው ያገኙትን የክፍያ መጠን አለመናገራቸውም ስምምነቱ ግልፅ በሆነ መስፈርት የተካሄደ አለመሆኑን ይጠቁማል፡፡ ማን በምን መስፈርት በምን ክራይቴሪያ ተመረጡ የሚለው ጨለማ የዋጠው መሆኑና ከጀርባው ያሉ ጠቋሚችና ደላሎች መኖራቸው ደግሞ የአርቲስቶቹ ክፍያ የእነርሱ ብቻ አለመሆኑን ያመላክታል፡፡ ይህንን ተከትሎ አርቲስቶችን ለንግድ አሻሻጭነት የመምረጥና የመጠቀም ግልፅነቱ የት ድረስ ነው የሚል ጥያቄ ይደፈጥራል፡፡

የክብር አምባሳድርነት ስያሜ በሙያ በህዝብ ዘንድ ባለ ክብርና ዝና ላይ ተመስርቶ የሚገኝ እድል በመሆኑ አርቲስቶቹ ከዚሁ ስምና ዝና ጋር በተያያዘ በግል ነጻነታቸው ላይ የተወሰነ ገደብ ለማድረግ ይገደዳሉ፤ እንደፈለጉ በነጻነት መንቀሳቀስ አልባሌ ቦታ መገኘትና ከህብረተሰቡ ባህልና ወግ ወጣ ያሉ ድርጊቶችና አልባሳትን ጭምር ከመጠቀም መታቀብን ሊያካተትት ይችላል፤ ይህንን ቀይ መስመር መተላለፍ ኪሳራው የአርቲስቱን ስምና ዝና ብቻ ሳይሆን የሚነካው ብራንድ አምባሳደር የተሆነለትን ድርጅት ጭምር ነው፤

አርቲስቶች ብራንድ አምባሳደር ሲሆኑ የሚያስተዋውቁት ምርት ወይም አገልግሎት ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ አስቅድመው መመርመር ይኖርባቸዋል፤ አለበለዚያ የተዋወቀው ምርት ወይም አገልግሎት ብልሽት ቢኖረው ጥራቱን ያልጠበቀ ቢሆን አልያም ሰሞኑን እንደምንሰማው ይገነባሉ የተባሉ ቤቶች ሳይገነቡ ቢቅሩ አለፍ ሲልም ምዝበራ ቢያጋጥም የእነዚሁ የምርት አሻሻጭ አምባሳደሮች ስም አብሮ መነሳቱ የማይቀር ነው፡፡ የብራንድ አምባሳደርነት በጎ ገጽታው ክብርና ዝና የሚያመጣ የመሆኑን ያህል አርቲስቶቹ ገንዘባቸውን ከተቀበሉ በኋላ ሲያስተዋውቁት የነበረው ምርት ወይም አገልግሎት በህብረተሰቡ ላይ ጎዳት ‹አመጣ› ሲባል አልሰማሁም አላየሁም የሚሉተ ነገር አነጋግሪ ነው፤ ይህ ሲሆን በተደጋጋሚ ታይቷልና፤ የብራንድ አምባሳደርነት ሲሰየሙ ለጋዜጣዊ መግለጫና ለፎቶ ስነስርዓት በቦታው ላይ ደምቀው የሚታዩተ አርቲስቶቹ ችግር ተከሰተ ሲባሉ ስልካቸውን አያነሱም፤ ተፈልገውም አይገኙም፤ ምናልባት በአጋጣሚ ከተገኙም ‹የብራንድ አምባሳደርነቴን እኮ ካቆምኩ አመት አልፎኛል› ሊሉ ይችላሉ፤ አንዳንዶቹ የክብር አምባሳደር ተደርገው ሲሾሙ ስለ ድርጅቱ መወድስ ካቀረቡ በኋላ ችግሩ ሲመጣ ‹እንደዚ መሆኑን አላውቀውም!› ይላሉ፡፡›ይህ በተለይ ለንግድ አሻሻጭነት ሃላፊነት በተቀበሉና ሲጠቀሙ በነበረሩ አርቲስቶች ዘንድ በስፋት የሚታይ ክስተት ነው፤

የዚህ አይነት ክስተቶች በቀጣይነት ይከሰቱ አይከሰቱ በሂደት የሚታይ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ አርቲስቶች የንግድ ብራንድ አምባሳደር ሆነው ለመስራት ከተለያዩ ድርጀቶች ጋር ሲፈራረሙ ታይተዋል፤ እንደ አብነትም አንጋፋው አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ የኪንግደም ሪል ስቴት አምባሳደር ሲሆን ሌላዋ ተወዳጅ አርቲስት መሰረት መብራቴ ደግሞ በሜትር ታክሲ አገልግሎት የዋን ራይድ አምባሳደር ሆናለች፤ በበርካታ የፊልም ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ከማይክሮ ፋይናንስነት ወደ ባንክነት ያደገው የፀደይ ባንክ አምባሳደር ሲሆን የሞጋቾች ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ፕሮዲውሰርና ተዋናይ አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾማታል፡

፡ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የዲጅታል እቁብን ለማስተዋወቅ ብራንድ አምባሳደር ሲሆን አርቲስት ሃና መርሀፅድቅ የአልሳም ፕሮፐርቲስ ብራንድ አምባሳደር ሆናለች፡ ፡ አርቲስቶቹ በብራንድ አምባሳደርነታቸው ወቅት የሚሰሩት ስራ በቀጣይነት የሚታወቅ ሆኖ ስያሜው ይፋ በተደረገበት ወቅት በየድርጅቶቹ የተገለጸው ዜና ምን ይመስላል፤………

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe