አርጀንቲና ለአለም ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች

በ2026 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ አርጀንቲና ብራዚልን 4 ለ 1 አሸነፈች።
ሌሊት 9 ሰአት ላይ በቦነስ አይረስ ጨዋታዋን ያደረገችው አርጀንቲና ትልቁን ደርቢ በማሸነፍ 4 ጨዋታ እየቀራት በትልቁ መድረክ መሳተፏን አረጋግጣለች።
በሙመንታል ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁሊያን አልቫሬዝ፣ ኢንዞ ፈርናንዴዝ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር እና ጁሊያኖ ሲሞን የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።
ማቲያስ ኩንሀ የብራዚልን አንድ ግብ አስገኝቷል። አንደ ሊዮኔል ሜሲ፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ፓውሎ ዲባላ አይነት ወሳኝ ተጫዋቾችን በጉዳት ሳይዝ የገባው ስብስብ ከጨዋታ ብልጫ ጋር የምንጊዜም ተቀናቃኙን አሸንፏል።
በ115ኛው ደርቢ በምድቡ 10ኛ ጨዋታዎን ያሸነፈችው የአለም ሻምፒዮኗ ሀገር በ31 ነጥብ ስትመራ ካደረገቻቸው 14 ጨዋታዎች 6ቱን ብቻ ያሸነፈችው ብራዚል ከተቀናቃኟ በ10 ነጥብ ዝቅ ብላ ወደ 4ኛ ደረጃ ዝቅ ለማለት ተገዳለች።
6 ሀገራት በቀጥታ በሚያልፉበት ማጣሪያ ቬንዙዌላ ፔሩን 1 ለ 0 ስታሸንፍ ኮሎምቢያ ከፓራጓይ ሁለት አቻ እንዲሁም ቺሊ ከኢኳዶር 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe