አስር ኢትዮጵያውያን ሴቶች በአፍሪካ የህዝብ ግንኙነት ሳምንት ጉባኤ ተመረጡ

የአፍሪካ ግሎባል ፒአር ሳምንት የአፍሪካን ታሪክ በመቅረጽ እና አህጉሪቱን በአለም መድረክ ላይ ከፍ በማድረግ ላይ ያለ መድረክ ነው። የአፍሪካን እድገት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነትና ማንነትን ለማጠናከር የህዝብ ግንኙነት ሙያ  ያለውን ክፍተኛ አስተዋፅኦ  ለመዳሰስ መንግስታትን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ስራ ፈጣሪዎችን፣ የድርጅት መሪዎችን፣ ደራሲያንን፣ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን አንድ ላይ የሚያሰባስበው የአፍሪካ ፒአር ሳምንት  በኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚከናወን ሁነት ሲሆን በዘንድሮው ፕሮግራም ላይ አስር ኢትዮጵያውያን እንስቶች በምርጥ የህዝብ ግንኑነት ሙያ ዘርፍ ታጭተዋል፡፡

ከመላው አፍሪካ የተወጣጡ ባለሙያዎች በሚታደሙበት በዚህ ዝግጅት ላይ ከየሃገሩ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ምርጥ ሴት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በእጩነት የተመረጡ ሲሆን በኢትዮጵያ የ PR ኢንዱስትሪን በመምራት ከሚገኙት ከፍተኛ ሴቶች መካከል እውቅና ያገኙት እነዚህ ባለሙያዎች በፈጠራ እና ስትራቴጂካዊ እድገት ግንባር ቀደም ናቸው ይላል በአፍሪካ ፒአር ሳምንት ድረ ገጽ ላይ የወጣው ፅሑፍ።

ከኢትዮጵያ እውቅና ያገኙት አስሩ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው።
•⁠ ⁠ራሄል ዘውዱ ከበደ፣ የኮሙኒኬሽን ስፔሻሊስት፣ USAID ኢትዮጵያ
•⁠ ⁠ሳምራዊት ግርማ፣ ከአልኮል ነፃ መጠጥ የብራንድ ምድብ አስተዳዳሪ፣ ሄኔከን ኢትዮጵያ ኩባንያ።
•⁠ ⁠ዮዳን ጥላሁን፣ የፍላውለስ ኢቨንትስ፤ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ፣
•⁠ ⁠ዊን ኤም.፣ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን
•⁠ ⁠ሃና አትናፉ፣ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
•⁠ ⁠ቢልሌኔ ስዩም ወ.፣ የፕሬስ ሴክሬታሪ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
•⁠ ⁠ኢትዮጲስ ታደሰ፣ DTM፣ PMP፣ የኮሙኒኬሽን ስፔሻሊስት
•⁠ ⁠ኤልሻዳይ ገበየሁ፣ የኮሙኒኬሽን ኦፊሰር በዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ
•⁠ ⁠ራህዋ ገብረመስቀል፣ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስፔሻሊስት
•⁠ ⁠ራሄል አሰፋ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ማርኬቲንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

እነዚህ ባለሙያዎች የአፍሪካን የወደፊት ሁኔታ እንዴት እንደሚቀርጹ እና ድምጿን በአለም መድረክ ላይ እንደሚያሳድጉ በመድረኩ ላይ ሰፊ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቀዋል፡፡

የአፍሪካ የሕዝብ ግንኙነት ሳምንት 2026 ከነሐሴ 26-28 በናይሮቢ ኬንያ  የሚካሄድ ሲሆን የአህጉሪቱን ታሪክ፣ ዲጂታል ስትራቴጂ እና የልማት እቅድ ለማስተዋወቅና ለመቅረጽ ባለሙያዎችን የሚያሰባስብ ዝግጅት ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe