አባስ አራግቺ አሜሪካ ካጠቃችን ራሳችንን የመከላከል ሙሉ መብት አለን አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የሆነ የአሜሪካ ወታደራዊ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት የኢራን ባለስልጣናት ዳግም ሐሙስ ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚሁ ንግግር ኢራን አዲስ ግጭትን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስፋ አለ ተብሏል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ትላንት እንደተናገሩት በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ዳግም ለሚመጀመረው ንግግር ሊደረስበት የሚችለውን ስምምነት ዝርዝር ሁኔታ እየቀረጹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የድርድሩ አመቻች የሆነችው ኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ንግግሮች ሐሙስ በጄኔቫ እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጥረት ለማድረግ አውንታዊ ግፊት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቅርቡ የአሜሪካ ልዩ መልክተኛ ስቲቭ ዊትኮቭ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ለምን ለፍላጎታቸው ተገዥ እንዳልሆነች እንደጠየቋቸው መናገራቸውን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ እኛ ኢራናዊያን ስለሆንን ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት ዊትኮቭ ትራምፕ ኢራን ይህ ሁሉ ጫና እየተደረገባት አልበገርም ለምን እንዳለች ማወቅ እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር፡፡ አራግቺ ለዚህ የትራምፕ ጥያቄ የሚሆን ምላሽ ነው በኤክስ ገጻቸው ላይ የለጠፉት፡፡
ኢራን ከወራት በፊት የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞን ያስተናደችበት መንገድ ከዋሽንግተን ጋር ወደ አዲስ ውጥረት እንዳስገባት ይታመናል፡፡
አባስ አራግቺ አሜሪካ ካጠቃችን እራሳችንን የመከላከል ሙሉ መብት አለን አሜሪካ ይህንን ካደረገችም፤በቀጠናው ያሉ የአሜሪካ ንብረቶች በሙሉ የእኛ የጥቃት ኢላማ መሆናቸው የማይቀር ነው በማለት ደጋግመው ተናግረዋል፡፡
ነገሮች በእንዲህ አይነት ውጥረት ላይ ቢገኙም በተመሳሳይ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ጎን ለጎን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁለት አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ተዋጊ ጄቶችንም ልካለች፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe