አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ኤልጎይባር አገር አቋራጭ ውድድር አሸነፈ

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ኤልጎይባር ሁዋን ሙጌርዛ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፈ፡፡
አትሌት ሰሎሞን ርቀቱን በ33 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ በመጨረስ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል፡፡
በርቀቱ ትውለደ ኢትዮጵያዊው እና ለባህሬን የሚሮጠው ብርሃኑ ባለው 2ተኛ ሲሆን÷ ስፔናዊው አዴል ሜካል 3ኛ ሆኖ ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ኒውስ ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ መርሐ ግብር በሴቶች የስምንት ኪሎ ሜትር ውድድር ኤርትራዊቷ አትሌት ራሄል ዳንኤል በ25 ደቂቃ ከ45 ሰኮንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡
በዚሁ ውድድር ኬኒያዊቷ አትሌት ኤዲና ጄቢቶክ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ዊንፍሬድ ያቪ ከባህሬን ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡
SourceFBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe