አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተለት

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተለት።

አንጋፋው አትሌት ፤ በአትሌቲክስ ዘርፍ ባበረከተው ሀገራዊ አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተለት።

ቀነኒሳ ሀገሩን ወክሎ በተካፈለባቸው ውድድሮች የሀገሩን #ኢትዮጵጵያን ስም ከፍ በማድረግ ታሪክ ፅፏል።

ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በሀገር ልማት እና በኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

አትሌት ቀነኒሳ በቆጂ ሆቴል፣ በአሰላ ሆቴልና የገበያ ማዕከል፣ በአዲስ አበባ ሆቴል፣ በአዳማ የገበያ ማዕክል በማስገንባት ለአካባቢው እና ለሀገሩ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ባበረከተውና እያበረከተ ባለው ስራ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶለታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe