አቶ ስብሀት ነጋ በግል ሀኪማቸው እንዲታከሙ ፍርድ ቤት አዘዘ!

የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ተሰይም የእነ ስብሀት ነጋ እና ሌሎች 2 መዝገቦችን ተመልክቷል።

አቶ ስበሀት ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት ጠበቆች ከዚህ ቀደም በፖሊስ ሆስፒታል ቢታከሙም ከህመማቸው አንፃር የሚመጥን እንዳልነበር አስረድተዋል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት ክትትል ያደርጉበት በነበረው አዲስ ህይወት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲፈቅድ ችሎቱን ጠይቀዋል።

የህገመንግስቱ አንቀፅ 21/2 መሰረት ተጠርጣሪው በግል ሀኪም ቢታከሙ የሚከለክል ሁኔታ አላየሁም ያለው ችሎቱ የግል ሀኪማቸው የህክምና መሳሪያዎቹን ይዞ ባረፉበት ቦታ እንዲያክማቸው አዟል።

የህመማቸው ሁኔታ ከፍተኛ መሳሪያውችን የሚጠይቅ ከሆነ ደግሞ ሀኪማቸው በችሎት ቀርቦ ቃለመሀላ ከፈፀመ በኋላ አስፈላጊው እጀባ ተደርጎላቸው በሆስፒታል ሆነው እንዲታከሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ይህ የማይሆን ከሆነ የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውም የተጠበቀ መሆኑን ችሎቱ አሳስቧል።

በሌባ በኩል የፌደራል ፖሊስ ባለፉት የምርመራ ቀናት የ85 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን እና የጦር መሳሪያዎችን ማሰባሰቡን ለችሎቱ ገልጿል።

ሆኖም ተጨማሪ የምርመራ ስራዎች ስለሚቀሩት 14 ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ምርመራው በጅምላ መሆን የለበትም በማለት ተቃውመዋል።

ይህን ሁሉ ጊዜ ለምርመራ ከተሰጠ በኋላ አሁንም በጅምላ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ የለበትም ብለዋል።

ማን ምን አይነት ወንጀል እንደፈፀመ በግልፅ ሊቀመጥ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ፖሊስ የእያንዳንዱን ወንጀል ለይቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠው ችሎቱ ተጨማሪ 13 ቀን ፈቅዷል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe