አቶ ስዩም መስፍን የባንክ ሂሳባቸውን ለማስመርመር ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

የግንቦት 20ን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም ምስፍን በዚህ ክብረ በዓል ዕለት በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት አንድ ነገር ቃል ለመግባት እወዳለሁ በማለት የባንክ ሂሳባቸውን ለማስመርመር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

Read also:‹በወረርሽኙ ምክንያት የኢኮኖሚ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል› ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  

አቶ ስዩም ይህንን ሲሉ ግን አንድ ነገር በቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው ነው፤ ይኸውም በሁሉም ባንኮች ያለው የባንክ ሂሳባቸው ሊመረመር የሚችለው ስልጣን ላይ ያሉት  የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም የባንክ ሂሳብ የሚመረመር ከሆነ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የባንክ ሂሳብ ቢመረመር የማን ሂሳብ ከፍተኛ እንደሆነና ማን ቢሊኒየር እንደሆነ ይታወቃል ያሉት አቶ ስዩም ይህ የሚደረግ ከሆነ የእሳቸው ብቻ ሳይሆን የሁሉም የህወሃት አመራሮች ሂሳብ  ወደ ኋላ ሰባት ትውልድ ድረስ በስማቸው ያለ ሂሳብ ሊመረመር  ይችላል ብለዋል፡፡

Read also:የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 27 ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታወቀ

የፌደራል የስነ ምንግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን የባለስልጣናት ሀብትን ድጋሚ ለመመዝገብ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን ይህንን በማያደርጉ ባላስልጣናት ላይ እርምጅ በአዋጁ መሠረት እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ዶ/ር አብይ አህመድ ለፌደራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ያስመዘገቡትን ሀብት ለህዝብ ይፋ እንዲያደርጉ በቁም ነገር መፅሄት ተጠቀይቀው ‹ይፋ ማድረግ ይቻላል፤ ነገር ግን  ማስመዝገቡ ምን ያህል እውነተኛውን ነገር ያሳያል የሚል ጥያቄ እንዳለ ጠቅሰው ማን ነው የዘረፈውን ሀብት በስሙ የሚያስመዘግባው › በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe