አነጋጋሪ የተባለ የደህንነት መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ ረቅቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ከደህንነት መስሪያ ቤት የተገኘን መረጃ ያለ ኃላፊ ፍቃድ መግለጽ እንደሚያስቀጣ የሚደነግግ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ

የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ያልሆነ ግለሰብ ያገኘውን መረጃ ከመስሪያ ቤቱ ኃላፊ ፍቃድ ውጭ ይፋ ካደረገ፤ በወንጀል ህግ እንዲጠየቅ የሚያደርግ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ የሚሰጥን መረጃ ጥቅም ላይ አለማዋል ቅጣት እንደሚያስከትልም ደንግጓል።

ሐሙስ ግንቦት 11፤ 2014 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የቀረበው ይህ የአዋጅ ረቂቅ፤ ከዘጠኝ ዓመት በፊት የወጣውን የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ የሚያሻሽል ነው። በኢፈዲሪ የወንጀል ህግ መሰረት ተጠያቂ የሚያደርጉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት አዲሱ አዋጅ፤ በነባሩ አዋጅ ላይ ያሉ ዘጠኝ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን አንድ አዲስ አንቀጽም እንዲጨመር አድርጓል።

የአዋጅ ረቂቁ ማሻሻያ ካደረገባቸው ድንጋጌዎች መካከል የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስልጣን እና ተግባራት እንዲሁም አደረጃጀት የሚመለከቱት አንቀጾች ይገኙበታል። የደህንነት መስሪያ ቤቱን በዳይሬክተር ጄነራልነት የሚመሩትን ኃላፊ ስልጣን እና ተግባር የሚመለከተው አንቀጽም እንደዚሁ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

 

በሌላ በኩል የደህንነት መስሪያ ቤቱን ለማቋቋም ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በህገ መንግስቱ እውቅና ያገኘውን የፕሬስ ነፃነት መብት የሚያጠብ እንደሆነና ሀሳብን በነፃነት መግለፅና የማሰራጨት መብት እንዳለ ሁሉ መረጃን ያለ ማሰራጨት መብትን ወንጀል አድርጎ መደንገጉ አስጊ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፤

በተለይም መረጃን ማሰባሰብና ለህዝብ ማሰራጨት ዋነኛ ስራቸው የሆኑ ጋዜጠኞች በስራ አጋጣሚ የደህንነት መስሪያ ቤቱን የተለመለከቱ  መረጃዎች ያለ መስሪያ ቤቱ ፈቃድ እንዳይዘግቡ በአዋጅ መከልከሉ ኢ ህገ መንግስታዊ ስለመሆኑ ነው የዘርፉ ምሑራን የሚገልፁት፤

ከዚህ በተጨማሪም ከደህንነት መስሪያ ቤቱ የሚሰጥ መረጃን ወይም መግለጫን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለህዝብ ማቅረብን ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት አስገዳጅ ማድረጉ የሚዲያ ተቋማትን ኤዲቶሪያል ነፃነት መጋፋት ስለመሆኑ ተገልፃል፤

በኢትዮጵያ መረጃ የማግኘት መብትን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ጥብቅ ሚስጥር ወይም ክላስፋይድ ተብለው በመንግስት ከሚለዩ መረጃዎች ውጭ ያሉ መረጃዎች ለህዝብ እንዲቀርቡ የሚፈቅድ ሲሆን የደህንነት መስሪያቤቱ እነዚህን መረጃዎች በአጠቃላይ ማንም እጁ የገባ ሰው  እንዳያሰራጭ በህግ መከልከሉ አነጋጋሪ ሆኗል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe