“በተለምዶ ‘አንዲት ሴት የመጀመሪያ ፍቅሯንና ድንግልናዋን የወሰደባትን ወንድ ትወዳለች’ የሚል የቆየ ዲስኩር አለ። ይህ ግን የወንዱ ዓለም የራሱን ክብርና ‘ኢጎ’ ለማስታመም የፈጠረው የሐሰት ተረት እንጂ፣ ሴቶች ድንግልናቸው ሲወሰድ የተለየ የወሲብ ጣዕም አስተናግደው ያንን ሰው እንዲወዱ የሚያደርጋቸው ምንም ዓይነት ተፈጥሯዊ ምክንያት የለም።
የመጀመሪያ ግንኙነት ወቅት የሚፈጠረው የደም መፍሰስና Hymen ሂደት ለሴቷ ከፍተኛ የሆነ የአካልና የአእምሮ ሕመም Physical and Psychological Pain እንጂ፣ ምንም ዓይነት “የተለየ የወሲብ ጣዕም” አይሰጣትም። ተፈጥሯዊ ሎጂክም ቢሆን፣ አንድ ሰው ስቃይና ሕመም የፈጠረበትን አካል ወይም ክስተት እንዲወድ የሚያደርግበት ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ምክንያት የለም።
እውነታው ያ ክስተት በአግባቡ በጥንቃቄ በስምምነት Consent ካልሆነ፣ የዕድሜ ልክ ጠባሳና የወሲብ ጥላቻን Aversion የሚወልድ ትልቅ ትሮማ ነው። አዎ፣ ተላምደውና ተገደው የሚኖሩ ይኖራሉ። ግን ቆም ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ዛሬ ላይ ወሲብን ብቻ ሳይሆን፣ ወንድን በአጠቃላይ የሚጠሉ ስንት ሴቶች አሉ? ‘ሚስት’ ስለተባሉ ብቻ የትዳር ግዴታቸውን ለመወጣት ሲሉ ብቻ የሚኖሩስ ስንት ናቸው? በማኅበረሰባችን ውስጥ ስለ እንዲህ ዓይነቱ እውነታ አይወራም፤ ነገር ግን በዚህ ስውር ስብራትና ትሮማ የሚሰቃዩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሴቶች አሉ።”
Sexual Trauma በሳይኮሎጂ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ረገድ፣ አንዲት ሴት መጀመሪያ ግንኙነት ስታደርግ ፍርሃት፣ ድንጋጤ እና ጭንቀት ውስጥ ከገባች፣ የአካል ክፍሎቿ ጡንቻዎች በራሳቸው ፍቃድ ሳይሆን ድንገት ይኮማተራሉ Involuntary Muscle Spasm ይህ የሕክምና ሁኔታ ቫጂኒስመስ Vaginismus ይባላል።
ይህ ችግር 90% የሚሆነው ከባዮሎጂ ይልቅ ከስነ-ልቦናዊ ፍርሃት የሚነሳ ነው። ማኅበረሰቡ “የመጀመሪያ ቀን ይደማል፣ ይቆርጣል፣ ያማል” እያለ የሰበከው ፍርሃት ሴቷ ላይ ከፍተኛ የጡንቻ መኮማተር ይፈጥራል። ያ ሲሆን ደግሞ ግንኙነቱ እጅግ አሰቃቂ ህመም ይኖረዋል፤ ይህም ህመም ድጋሚ ፍርሃትን ይወልዳል ይህ የፍርሃትና የህመም አዙሪት loop ይሆናል።
የመጀመሪያው ግንኙነት በስምምነት፣ በፍቅርና በእንክብካቤ ሳይሆን “በኃይል ከተከናወነ፣ የአንጎላችን ክፍል Amygdala ያንን ክስተት እንደ “አደጋ/ጥቃት” መዝግቦ ይይዘዋል። ከዚህ ክስተት በኋላ ሴቷ ወሲባዊ ፍላጎትን፣ ንክኪንና ወሲብን በአጠቃላይ የመጥላት፣ የመሸሽና የመጸየፍ Sexual Aversion ስነ-ልቦና ታዳብራለች። ወሲብ ለሷ የደስታ ምንጭ ሳይሆን፣ የስቃይና ፍርሃት ምክንያት ሆኖ ይቀርፃል።
ህመሙና ድንጋጤው እየቆየ ሲሄድ፣ ጥላቻው ከድርጊቱ ከወሲቡ አልፎ ወደ ፈጻሚው ወደ ወንዱ ጥላቻ ይሻገራል።
በማኅበረሰባችን ውስጥ “በትዳር ውስጥ ወሲብ መከልከል ኃጢአት ነው/ነውር ነው” ስለሚባል ብቻ፣ በዚህ ትሮማ ውስጥ ያሉ ሴቶች ግንኙነቱን አይቀበሉትም እንጂ አይቃወሙትም። ነገር ግን ድርጊቱ በሚፈጸምበት ሰዓት አእምሮአቸውን ከአካላቸው የመንጠል Dissociation ስነ-ልቦናዊ መከላከያ ይጠቀማሉ።
ሴቷ በአካል እዚያ ብትሆንም፣ በአእምሮዋ ግን ሌላ ቦታ ትሆናለች፤ ሙሉ በሙሉ ስሜቷን አጥፍታ ልክ እንደ አስከሬን ትሆናለች። ይህ በትዳር ስም የሚፈጸም ስውር የዕለት ተዕለት ጥቃት Silent Marital Trauma ነው።
በሳይኮሎጂ እና በሕክምናው ዓለም ይህ አንዲት ሴት ከደረሰባት የሕመም እና የስነ-ልቦና ጫና የተነሳ በአካል አብሮ መተኛትን ጨምሮ ወሲባዊ ንክኪዎችን ሙሉ በሙሉ የምትጠላበት እና የምትሸሽበት ሁኔታ ሴክሹዋል አቨርዥን ዲስኦርደር Sexual Aversion Disorder ይባላል።
ይህ በሽታ Disorder ያለባቸው ሴቶች ከወሲብ ድርጊት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ነገሮች—ንክኪን፣ መሳሳምን፣ አልፎ ተርፎም ከአንድ ወንድ ጋር በአንድ አልጋ ላይ መተኛትን—በከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት እና ጥላቻ ይሸሹታል።
በዚህ ጊዜ ሴቷ በህይወቷ ያለን ወንዱን ብትወደው እንኳ፣ ወደ አልጋ የመሄዱ እና የመነካካቱ ሂደት ላይ ሲደረስ ግን ሰውነቷ በከፍተኛ ፍርሃትና ጭንቀት Panic ይወጠራል። ድርጊቱ የሚታያት እንደ ፍቅር መግለጫ ሳይሆን፣ እንደ ጥቃት ነው።
ሳይኮሎጂ እንደሚያብራራው፣ አንዲት ሴት አብሯት ያለውን ወንድ ጋር መተኛት እንኳን የምትጠላው እሱን በግል ስለጠላችው ብቻ ላይሆን ይችላል፤ ይልቁንም አእምሮዋ ራሷን ከተጨማሪ ሕመም ለመጠበቅ የሚጠቀምበት የመከላከያ ዘዴ Defense Mechanism ነው። በአእምሮዋ ውስጥ “ወንድ ልጅ = ሕመም/ስቃይ” የሚል እኩልዮሽ ስለሚቀረጽ፣ ያንን ሕመም ላለመጋፈጥ ወንዱን እና sexual ግንኙነቱን በአጠቃላይ ማራቅ ብቸኛው አማራጭ ሆኖ ያገኘዋል ማለት ነው።
ይህ በትዳርም ውስጥ ሴቶች ፍላጎታቸው ሳይጠየቅ፣ በአካልም ሆነ በስነ-ልቦናዊ ጫና ተገደው ወሲብ እንዲፈጽሙ ሲደረግ የሚፈጠር ፍጹም የረጅም ጊዜ የስነ-ልቦና ቀውስ Marital Sexual Trauma ነው።
“ይህ ዓይነቱ የስነ-ልቦና ስብራት Trauma ብዙ ጊዜ ከትዳር ውጭ በተደፈሩ ሴቶች ላይ ብቻ እንደሚከሰት ተደርጎ ነው የሚወራው። ነገር ግን በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ በትዳር ውስጥ ወሲብን ማስገደድ እንደ ‘ግዴታ’ ነው የሚቆጠረው። ሲጀመር ‘ትዳር የሚመሠረተው ለመዋለድና ለወሲብ አይደለም እንዴ? ታዲያ ለምን እምቢ ትላለች? ያገባት እኮ ለዚሁ ነው!’ የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶች ይደረደራሉ። ማኅበረሰባችን ‘ባሏ ስለሆነ መብቱ ነው፣ ሚስት ስለሆነች ግዴታዋ ነው’ በሚል ሰበብ፣ በትዳር ውስጥ የሚፈጸመውን ይፋዊ መደፈርና የቤት ውስጥ ጥቃትን እንደ ወንጀል አይቀበለውም።
ነገር ግን በሳይኮሎጂ እና በሕግ እይታ ይህ ድርጊት ‘በትዳር ውስጥ መደፈር’ Marital Rape በመባል ይታወቃል። አንዲት ሴት በትዳር ውስጥ እየኖረች፣ ባሏም ቢሆን ሳትፈልግና ያለፍቃዷ የምታስተናግደው የግዳጅ ወሲብ ከፍተኛ የአካልና የመንፈስ ሕመም ይፈጥርባታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ወሲብን ብቻ ሳይሆን፣ ባሏንና ወንድን በአጠቃላይ መጥላት ትጀምራለች። ይህ ድርጊት በሴቶች ላይ የሚያስከትለው የስነ-ልቦና ቀውስ እጅግ አስከፊ ነው!
“አንዲት ሴት የመጀመሪያ ፍቅረኛዋን የምትወደውና የምታስታውሰው ከሆነ፣ ማኅበረሰቡ እንደሚያስበው ድንግልናዋን ስለወሰደ ወይም ያንን ሕመም ስለፈጠረባት አይደለም።
“በተቃራኒው ግን፣ አንዲት ሴት የመጀመሪያ ፍቅረኛዋን በበጎ የምታስታውሰው ከሆነ፣ ማኅበረሰቡ እንደሚያስበው ድንግልናዋን ስለወሰደ ወይም ያንን ሕመም ስለፈጠረባት ሳይሆን”ይልቁኑ ያንን አስፈሪ የሕመም ስቃይ፣ ፍርሃትና ድንጋጤ በፍቅርና በእንክብካቤ ቀይሮ፣ አክብሮና ተንክባክቦ ሕመሟን ያስረሳትን፣ እሱንም ሆነ ወሲብን በደስታ እንድትቀበል ያደረጋትን ያንን የወንድ የፍቅር መንገድ Healing Approach ነው!”
“በሕይወት አጠገብህ ያለችን ሴት በአካልም፣ በአእምሮም ሆነ በወሲባዊ ሕይወቷ ደስተኛ ማድረግና እንድትወድህ ማድረግ ሳትችል ቀርተህ_ከእኔ በፊት የነበረውንና ድንግልናዋን የወሰደውን ሰው ስለምትወድ ነው’ እያልክ የራስህን ድክመት አታፅናና፣ ራስህንም አታታልል፤ ‘ኢጎህንም’ አታስታም!”
“የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ መሆን የጊዜ እና የአጋጣሚ ጉዳይ ብቻ ነው። ‘የመጀመሪያ’ ሰው ሊረሳ የማይችለው—በፈጠረው ሕመም፣ ጠባሳና ትሮማ Trauma አይደለም። አንዲት ሴት በሕይወቷ ውስጥ በፍጹም የማትረሳው እና ሁልጊዜም በክብር የምታስታውሰው ሰው_የአካልና የአእምሮ ደኅንነቷን የጠበቀ፣ ፍቅር የሰጣት፣ የተንከባከባት፣ እንዲሁም እራሷን እንድትሆን ፍፅምናንና ቅድስናን ሳይጠብቅ በልዩነት የወደዳትና የተቀበላት ወንድ ነው!” (Adoni)

