አንጀሊና ጆሊ እና ብራድ ፒት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ግዙፍ የህፃናት ሆስፒታል ሊያቋቁሙ ነው

የታዋቂዎቹ የሆሊዉድ ተዋንያን አንጀሊና ጆሊ እና ብራድ ፒት ፋውንዴሽን 2 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ በሳምባ ነቀርሳና ኤች አይ ቪ የተጠቁ ህፃናት ህክምና የሚያገኙበት ሆስፒታል በኢትዮጵያ ሊያቋቁም እንደሆነ አስታወቀ። ሆስፒታሉ ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ወስደው በሚያሳድጓት ዘሀራ ስም የሚሰየም ይሆናል።

በኢትዮጵያ የሚቋቋመው ሆስፒታል ፋውዴሽኑ በካምቦዲያ የመሰረተውንና ህፃናት ህክምና፣ ትምህርትና ማህበራዊ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሆስፒታል ሞዴል እንደሚያደርግም ተገልጿል።

አንጀሊና ጆሊ ምስረታውን በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ እንደተናገረችው ፋውዴሽኑ በኢትዮጵያ በሳምባ ነቀርሳና በ ኤች አይ ቪ ያለአግባብ ህይወታቸውን የሚያጡ ህፃናትን በመታደግ በካምቦዲያ ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያም የመድገም አላማ እንዳለው ተናግራለች።

ብራድ ፒት በበኩሉ ዘሃራ ኃላፊነት የምትሸከምበት እድሜ ላይ በደረሰች ጊዜ ሆስፒታሉን በማስተዳደር የተቋቋመለትን ተልዕኮ እንደምታስቀል ተስፋ እናደርጋለን ብሏል።

ጆሊ-ፒት ፋውንዴሽን ለ Global Action for Children እና ለ Doctors Without Borders ለያንዳንዳቸው 1 ሚለየን ዶላር በመለገስ ከ20 አመታት በፊት በሁለቱ ተዋንያን የተቋቋመ አለም አቀፍ ምግባረ ሰናይ ድርጅት  መሆኑን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe