አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ በተወለደ በ71 ዓመቱ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 11/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡
አርቲስቱ የእግር እሳት፣ ሥርየት፣ ሰው ለሰው፣ መንጠቆ ቴአትር እና ሌሎች የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በትወና መሳተፉን የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡
በአዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ የተወለደው አርቲስት እንቁስላሴ ÷በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጧል፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅ አገኘሁ የአንድ ወንድ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር፡፡
አርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ ከአባቱ ከአቶ ወ/አገኘሁ ኃይሌ እና ከእናታቱ ወይዘሮ ዘውድነሽ ብሩ በጥቅምት 27/1946 በአዲስ አበባ ከተማ መወለዱን የህይወት ታሪኩ ያትታል።
ከባለቤቱ ወይዘሮ አይናለም ወርቁ 3 ሴቶች እና 3 ወንድ ልጆች ያፈራ ሲሆን እንዲሁም 12 የልጅ ልጆችን አፍርቷል፡፡
የአርቲስት እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ በተወለደ በ71 ዓመቱ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 11/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ የቀብር ስነስርዓቱ ትናንት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቀጨኔ መድሐኒዓለም ቤተክርስትያን ተፈፅሟል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe