የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ፍርድ ቤት ሊያቆሙት ነው ተባለ፡፡ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲውን በህግ የምጠይቀው በትምህርት ዘርፍ አወቃቀር ላይ ቅሬታ ስላለን ነው ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ጉዳዩን የፈለጉበት ቦታ መውሰድ ይችላሉ የሚለወጥ ነገር አይኖርም ብሏል፡፡
በራስ ገዝነት ሂደት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነበሩትን ኮሌጆችና የትምህርት ፕሮግራሞች እየቀነሰና እያጠፈ በመምጣቱ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ናቸው በህግ ሊጠይቁት መሆኑን ያሳወቁት፡፡
የዩኒቨርሲቲው እርምጃ ተገቢ አለመሆኑንና በጉዳዩ ላይም የእነርሱ አስተያየት ያልተጠየቀበት በመሆኑ ቅሬታችንን ለዩኒቨርሲቲው ብናቀርብም ምላሽ ሊሰጠን አልወደደም ነው ያሉት፡፡ በዚህ የመጨረሻ ወደላሉት በህግ የመጠየቅ ሂደት ልናመነራ ነው ብለዋል፡፡
ኮሌጆቹ በመታጠፋቸው ምክኒያት የመረጥነውን ትምህርት ሳይሆን ሌሎች ትምህርቶችን እንድንማር የሚያደርገን በመሆኑ ውላችንን ዩኒቨርሲቲው እንዲያከብር ነው ጥያቄያችን ብለዋል፡፡
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከራስገዝ ሂደት ጋር በተገናኘ ከዚህ ቀደም የነበሩትን 11 ኮሌጆችን ወደ ስምንት መቀነሱ ይታወቃል፡፡
ከታጠፉት የድህረ ምረቃና የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርቶች ውስጥ ደግሞ አሁን በተማሪዎች ቅሬታ የተነሳበት የአገር ልማት ጥናት ኮሌጅ ሲሰጥ የቆየው የምግብ ደህንነት ጥናት ይገኝበታል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር ምክትል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ቅሬታውን በተመለከት ተማሪዎች ስለኮሌጅ መፍረስ አለመፍረስ አይመለከታቸውም፤ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡም ለፕሮግራም እንጂ ለኮሌጅ አይመዘገቡም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በትምህርቱ መጨረሻ ላይም ዲግሪ ሲያገኙ የሚሰጠው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንጂ የአንድ ኮሌጅ ዲግሪ አይደለም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ኮሌጅና ዲፓርትመንት የአስተዳደር መዋቅር እንጂ በራሳቸው ፕሮግራም አይደሉም፡፡ ፕሮግራሙ ባለቤትና ዲግሪው ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮግራሞቹ ሲዋቀሩ ሰፊ ውይይቶች እንደተደረጉነትና በዚህም መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ ሲሉ አንስተው፡፡ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ጉዳዩን ወደፈለጉበት ቦታ መውሰድ ይችላሉ ብለዋል፡፡//

