አወዛጋቢው አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ (አንችም ዜሮ ዜሮ) ይኖርበት በነበረው አሜሪካን ሀገር ህይወቱ ማለፉ ተሰማ

አወዛጋቢው አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ (አንችም ዜሮ ዜሮ) ይኖርበት በነበረው አሜሪካን ሀገር ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ ከድምጻዊነቱ ባሻገር በፖለቲከኛነቱ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡

አንችም ዜሮ ዜሮን ዘፍኖ ከሀገር ተሰዷል፡፡ ወደ ኤርትራም ተሻግሮ ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በኢትዮጽያ የመንግስት ለውጥ እንዲደረግ ፕሬዜዳንቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለመጠየቅና በዚያ ካሉ ታጋዮች ጋርም እቅድ ለምደፍ በአስመራ በረሃ ከ1 ወር በላይ ቆይቷል፡፡ በጊዜ ሂደት ነገሮች ተለውጠውም ሚሊኒየሙ ሊከበር ጥቂት ጊዘያት ሲቀሩት ይቃወመው ከነበረው መንግስት ጋር እርቅ አውርዶ በ1989 ከተሰደደ በኃላ በ1999 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ በዚሁ ወቅትም ከቁም ነገር መጽሔት ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡

አርቲስት ሰለሞን የመጀመሪያ ካሴቱን በ1978 ዓ.ም ከሰራ በኋላ ፋጡማ የተሰኘ ስራውም ለአድማጭ ማድረሱን በቃለ ምልልሱ ላይ ግልጾ ነበር፡፡

በመቀጠልም ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሊገባ ደርግ ስዓት እላፊ ያወጀበት ጊዜ ላይ አራዳ የሚል ዘፈን ያለበት ካሴት አውጥቶ ወቅቱ ግርግር ስለነበር ብዙ እንዳልተደመጠ እና ኋላ ላይ ግን በየሚዲያው ስለቀረበ ውጤታ መሆን መቻሉን ይፋ ተናግሮም ነበር፡፡

አርትስት ሰለሞን ከዜሮ ዜሮ በኋላ የሰራኋቸው ዘፈኖች ለገበያ ሳይሆን ለፖለቲካዊ አለማ ድጋፍ የሚሰጡ መሆናቸውንም አስታውቆ ነበር፡፡

በእነዚህ ስራዎችም ተጠቃሚ የሆኑት በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉት እንጂ እኔ አልነበርኩም ነበር ያለው፡፡ አርቲስቱ በ1999 ዓ.ም ድንገት ከፖለቲካ እራሴን አግልያለሁ ማለቱ በወቅቱ እጅግ መነጋገሪያ ነበር፡፡

ሐምሌ ወር 1999ዓ.ም ለቁም ነገር መጽሔት በሰጠው ኢንተርቪው ላይም ከዚህ በኋላ እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፤ህዝብንና መንግስትን ለማቀራረብ ነው የምስራው ሲል ነበር ምላሽ የሰጠው፡፡ በባህሪዬ ምላሹ ምንም ይሁን ምን ላመንኩበት ነገር እሞታለሁ ይህንንም ሳደርግ ኖሪያለሁ፡፡ ያመንኩበትን ነገር ግን አሁን ተቀምጬ ሳስበው ጥፋት እንደነበር አምኜበታለሁ፡፡ በፍርድ ቤት የተከፈተብኝ ክስ ሲነሳልኝ ህዝብንና መንግስትን ይቅርታ ጠይቄ ለመስራት ሀገሬ ገብቻለሁ ነበር ያለው በወቅቱ፡፡

ካፎቱ ይውጣ ጉራዴው ሳንጃው

ደም በደም ይሁን መረማመጃው

እሪ በል መርኬ እሪ በል ፒያሳ

ይጭስ ይጫጫስ አንዴ ተነሳ፡፡ እያለ ሲቃነቅን የነበረው አርቲስት ሰለሞን ያራመድኩት አቋም ትክክል አልነበረም አሁን ከዚህ እርቂያለሁ ነበር ያለው፡፡

በወቅቱም ሰለሞን ወደ ሀገሩ የተመለሰው ከመንግስት ጉርሻ ተሰጥቶት ነው፡፡ ወትሮውንም ቢሆን ሰለሞን ሙዚቃ አላዋጣ ሲለው ነው ወደ ፖለቲካው የገባው የሚል ተችት ይነሳብሃል ተብሎ ሲጠየቅ፡፡ ከመንግስት ምንም ያገኘሁት ነገር የለም፤ሙዚቃ አይችልም ለሚሉት ደግሞ እኔ ተሰጥኦየን አውቀዋለሁ ነበር ያለው፡፡

ይህ መንግስት ይኑር ሌላውም ይምጣ  በምንም አይነት ከእንግዲህ ወደ ፖለቲካ አልገባም ሲል ነበር በወቅቱ የገለጸው፡፡ ነገር ግን አርቲስቱ እስከ ህልፈቱ ድረስ ግን ከፖለቲካው አራቀም ነበር፡፡

ውጡ ተዝናኑ፡ይች አለም እንደሆነች በማናውቀው ቅጽበት ምን እንደሚፈጠር አናውቅምና ነገን ትተን፤ዛሬን እንዝናና ህይወታችን እናድስ የሚል መልዕክት በሶሻል ሚዲያው ላይ ካጋራ ከቀናት ልዩነት በኋላ ፋሲካን ከቤተሰቡ ጋር ውሎ አመሻሽ ላይ ህይወቱ እንዳለፈ ነው የተነገረው፡፡

አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ ከ1989 ጀምሮ ለረጅም ዓመታት ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ አድርጎ ነበር፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe