አውስትራሊያ ጉግል እና ፌስቡክ በገጾቻቸው ላይ ላሉ ዜናዎች ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያደርግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያውን ሕግ አወጣች፡፡
ሕጉን አሜሪካዊያኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በጥብቅ ተቃውመውታል፡፡
ባለፈው ሳምንት ከፌስቡክ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ሁሉንም ዜናዎች ከአውስትራሊያውያ ቢያግድም ከመንግስት ጋር ከተደረገ ድርድር በኋላ ውሳኔውን በዚህ ሳምንት ቀይሮ ነበር፡፡
ድርድሮቹን ተከትሎም ሕጉ አዲስ ማሻሻያዎችን በማፅደቅ ፌስቡክ እና ጉግል ለኮዱ ተገዥ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ሆኖም ሁለቱም ኩባንያዎች ከአዲሱ ሕጉ ውጭ ለአንዳንድ ትልልቅ የአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ቃል ገብተዋል፡፡
ውሳኔዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ እንደተስማሙ ተደርጎ በስፋት ተወስዷል።
የአውስትራሊያ ሕግ ለሌሎች አገራትም ከተመሳሳይ ዲጂታል መድረኮች ክፍያ ለማግኘት እንደ ሙከራ ተደርጎ ታይቷል ፡፡
የተሻሻለው ሕግ ቀደም ሲል ሴኔቱን ካለፈ በኋላ በተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት ነው የፀደቀው፡፡
ፌስቡክ እና ጉግል “በመሠረቱ” በይነመረብ እንዴት እንደሚሠራ በተሳሳተ መንገድ ተከራክረዋል፡፡
ሕጉ ምን ያደርጋል?
ሕጉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የዜና ድርጅቶች የክፍያ ስምምነቶችን እንዲደራደሩ ያበረታታል፡፡ ንግግሮች ካልተሳኩ ወደ ገለልተኛ የግልግል ዳኝነት ሊሄዱ ይችላሉ፡፡
ለዜና ድርጅቶች የበለጠ አቅም ስለሚሰጥ በፓርቲዎቹ መካከል “ፍትሃዊ” የድርድር ሂደት ይደረጋል ሲል መንግስት ተከራክሯል፡፡
የአውስትራሊያ ውድድር እና የሸማቾች ኮሚሽን የዜና ድርጅቶች እንደ ጉግል እና ፌስቡክ ባሉ ኩባንያዎች ላይ ጥገኛ ስለሆኑ እስከአሁን ድረስ የመደራደር አቅማቸው አነስተኛ ነው ይላል፡፡
ተንታኞች እንደሚሉት በዋጋ ላይ የሚነሱ ማናቸውም ክርክሮች በግልግል ዳኝነት መፈታታቸው የዜና ድርጅቶችን ይጠቅማል፡፡
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ በአሠራራቸው ላይ ለውጦችን ካደረጉ ለመገናኛ ብዙሃን እንዲያሳውቁ ሕጉ ያስገድዳል፡፡
የተሻሻለው ሕግ ለዜና ድርጅቶች ከመተግበሩ በፊት መንግሥት ለጋዜጠኝነት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ እንዲመረምር ያስገድዳል ፡፡
በዚህም ፌስቡክ እና ጉግል የድርድር ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ማምለጥ ይችላሉ ማለት ነው፡፡
መንግስት ሕጉን ተግባራዊ እንዲያደርግላቸው ለማድረግ የአንድ ወር ማሳወቂያ ጊዜም መስጠት አለበት፡፡
ጉግል እና ፌስቡክ ምን አሉ?
የቴክኖሎጂ ተቋማቱ ታዳሚዎችን ከመድረኮቻቸው ወደ ዜና ጣቢያዎቹ በመመለስ የዜና ድርጅቶቹን ቀድሞውኑም እየረዳን ነበር ብለው ይከራከራሉ፡፡
ሰዎች ዜና በቀላሉ እንዲያገኙ ፌስቡክ እና ጉግል ይረዷቸዋል ይላሉ፡፡
ሁለቱም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአውስትራሊያ መንግስት ሕጉን እንዲያሻሽል ሲያግባቡ እና ከአገር ውስጥ የዜና ኩባንያዎች ጋር ውል ለመፈጸም ሲሠሩ ነበር፡፡
ጉግል ዋነኛ የመረጃ መፈለጊያው ከአውስትራሊያ እንደሚያስወጣ ቢገልጽም እንደ ናይን ኢንተርቴመንት እና ሰቭን ዌስትሚዲያ ካሉ የሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃ ጋር 47 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ስምምነት ደርሷል፡፡
እንዲሁም ከሩፐርት ሙድሮክ የዜና ኮርፖሬሽን ጋር ይፋ ባልተደረገ ዋጋ ስምምነት ተፈራርሟል ፡፡
ፌስቡክ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ የአውስትራሊያ የዜና ገጾች የማይገኙ ቢሆንም በዜና ይዘት ላይ የጣለውን እገዳ እንደሚቀለብስ ቃል ገብቷል፡፡
ከዚያን ወዲህም ከሰቭን ዌስት ሚዲያ ጋር ስምምነት የደረሰ ሲሆን ከሌሎች የአውስትራሊያ የዜና ተቋማት ጋር እየተነጋገረ ይገኛል፡፡
አሁን ምን ይሆናል?
ፌስቡክ ባለፈው ሳምንት የአውስትራሊያ የዜና ይዘቶችን ባለመያዙ በአውስትራሊያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከባድ ትችቶችን አስነስቶበታል፡፡
ኩባንያው ቁልፍ የጤና እና ድንገተኛ አደጋ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ ዜና-ያልሆኑ ገጾችን ጭምር በማስወገድ ከሚገባው በላይ መጓዙን አምኗል።
ጠንካራ እርምጃው እንደ ካናዳ፣ እንግሊዝ እና አውሮፓ ሕብረት ያሉ እና ከአውስትራሊያ ጋር ተመሳሳይ ፍላጎት ላላቸው ሌሎች የሕግ አውጭዎች የማስጠንቀቂያም ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ብዙዎችን ዜናዎችን ከበይነ መረቦች የማንበብ ልምዳቸው በመጨመሩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለዜና ተቋማቱ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚጠይቅ ዓለም አቀፍ ግፊት ጨምሯል።
ባላቸው ከፍተኛ ጉልበት ለከፍተኛ ምርመራ የተጋለጡ ሲሆን የተሳሳተ መረጃን እና አላግባብ የሆነ አጠቃቀምን እንዲዋጉ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው፡፡